Saturday, 13 October 2018 11:27

ሁለተኛው ጣና የሶሻል ሚዲያ አዋርድ ተጠናቀቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

· ዳንኤል ክብረት በሥነ ፅሑፍ፣ ጌጡ ተመስገን በፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ዘርፎች አሸንፈዋል
· ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ5 አሸናፊዎች የሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት እድል ሰጥቷቸዋል
    
     በዘመራ መልቲ ሚዲያና በሰለሞኒክ ኢንተርቴይንመንት፣ በየዓመቱ የሚዘጋጀውና ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር የሚጠቀሙ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን አወዳድሮ የሚሸልመው ሁለተኛው ጣና የሶሻል ሚዲያ አዋርድ ሥነሥርዓት፣ የዛሬ ሳምንት በባህር ዳር ከተማ፣ በብሉናይል ሪዞርት በድምቀት የተከናወነ ሲሆን ከ16ቱ ዘርፎች መካከል በሥነ ፅሁፍ ዘርፍ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ በፈጣን ወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ ዘርፍ፣ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፤ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ፣ ጋዜጠኛ ጌትነት ተመስገን፤ በታሪክ ዘርፍ፣ጋዜጠኛ ኢዮብ ዘለቀ አሸናፊ በመሆን ተሸልመዋል፡፡ በወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ፣የኛ ቲዩብ፤በማህበራዊ ሚዲያ ባበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ ደግሞ የድሬ ቲዩብ ቢኒያም ነገሱ  ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በጤና ዘርፍ አለ ዶክተር 8809፣ በስነ ጥበባዊ ምስሎችና ትርክቶች ሰዓሊና ቀራፂ ኢያዩ ገነት፣ በፎቶግራፍ ዘርፍ ኢትዮጲክስ እና በሌሎች ዘርፎችም አሸናፊዎች ተሸልመዋል፡፡
ሽልማቱን ያሸነፉት ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣ ጋዜጠኛ ኢዮብ ዘለቀ፣ ጋዜጠኛ ጌትነት ተመስገን በአጠቃላይ ለአምስት አሸናፊዎች በጥናትና ምርምር ዘርፍ የዕለቱ አሸናፊ የሆነው አንጋፋው ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ዲግሪ ነፃ የትምህርት እድል አጎናፅፏቸዋል፡፡

Read 978 times