Print this page
Saturday, 13 October 2018 10:33

ከመጠን ያለፈ ውፍረት …በህጻናት…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 የህጻናት (ከ0-5) አመት ድረስ ያለው ከመጠን በላይ መወፈር እንደውጭው አቆጣጠር ከ1990 እስከ 2016 ድረስ ባለው ጊዜ ከ32 ሚሊዮን ወደ 41 ሚሊዮን ቁጥር ጨምሮአል፡፡ በዚሁ ወቅት በአለም የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት የአፍሪካ አካባቢ ብቻ ተለይቶ ሲታይ የህጻናቱ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከ4 ሚሊዮን ወደ 9 ሚሊዮን አድጎአል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የህጻናት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከተመዘገበባቸው የአለማችን ክፍሎት በማደግ ላይ ባሉት ሀገራት ያለው ከ30% በላይ ካደጉት ሀገራት ይልቅ ከፍ ብሎ ይገኛል፡፡ ሁኔታዎች አሁን ባሉበት የሚቀጥሉ ከሆነም የህጻናቱ እና ወጣት ልጆች ከመጠን በላይ ውፍ ረት በአለም አቀፍ ደረጃ በ2025 እስከ 70 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል የአለም የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡
ሁኔታዎችን ለመለወጥ ምንም ጥረት ካልተደረገ ገና የተወለደ ህጻና ከመጠን በላይ ውፍረት ይዞት መታየቱ በቀላሉ የሚቋረጥ ሳይሆን በወጣትነቱም ይሁን ትልቅ ሰው ሲሆን ውፍረቱ የሚቀጥል ስጋት መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡
ከልክ ያለፈ ውፍረት በሕጻንነት ጊዜ ሲታይ እንደምቾት ወይንም ደስታ ተደርጎ የሚቆጠር ሳይሆን ከፍተኛ የጤና ችግር ነው በሚል ሊጨነቁለት የሚገባ ነው፡፡ ምናልባትም እንደስኩዋር የልብ ሕመም የመሳሰሉትንም ሕመሞች እንደሚያስከትል ከወዲሁ መገመቱ እና ውስብስብ ወደሆነ የውስጥ ደዌ ሕመም እንዳያመራ እና ገና ባልጠና ሰውነታቸው ለከፋ ችግር እንዳይጋ ለጡ አስቀድሞ ማሰብ እና ባለሙያን ማማከሩ ይበጃል፡፡
አንድ ሕጻን ልጅ ሲወለድ ጀምሮ እስከ 6/ወር ድረስ ከእናት ጡት በስተቀር ሌላ ተጨማሪ ምግብ አለመስጠት ሕጻናቱን ከመወለዳቸው ጀምሮ አግባብ ላልሆነ ውፍረት እንዳይጋለጡ ይረዳቸዋል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት ባወጣው ዘገባ በሕጻንነት የሚከሰት ከልክ ያለፈ ውፍረት ከሚያስከት ለው የጤና ችግር የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡
የልብ ሕመም፤
በሰውነት ውስጥ የሚመረተው ኢንሱሊን ያለመመረት ችግር እና የስኩዋር ሕመም እንዲከሰት ምልክት ማሳየት፤
የመገጣጠሚያ አካላት ወይንም የጡንቻዎች ሕመም፤
በተወሰኑ የሰውነት ክፍሎች ላይ የካንሰር ሕመም መከሰት፤
አካል ጉዳተኝነት፤
ሕጻናቱን ከልክ ላለፈ ውፍረት ሊያጋልጣቸው የሚችል በርካታ ምክንያት የሚኖር ሲሆን ዘገባው ከጠቀሰው መካከል ሕጻናቱ በተረገዙበት ወቅት ወይንም የሚወለዱበት እና የሚያ ድጉበት አካባቢ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኩዋር ሕመም ለተ  ረገዘው ልጅ በሚወለድበት ጊዜ ከፍ ያለ ክብደት እንዲኖር እና በወደፊት ሕይወቱም ላይ አለአግባብ መወፈር እንዲኖር ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ሕጻናቱ የሚመገቡትን ነገር በሚመለከት ገና ከጅምሩ ማሰብ የሚገባ ሲሆን የተወለዱ ልጆች ጤናማ የሆነ አመጋገብ እንዲኖራቸው ማድረግ ከሁሉም ወላጅ ወይንም አሳዳጊ የሚጠበቅ ነው፡፡ የተወለዱ ልጆችን ከፍተኛ ስብ ያለበት ከፍተኛ የስኩዋር መጠን ያለው ወይንም ከፍተኛ ጨው ያለበት ምግብ …መመገብ በሕጻንነት ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዲኖር መንገድ ይከፍ ታል፡፡
የተመጣጠነ ምግብን በሚመለከት በቂ መረጃ አለማግኘት ወይንም አስፈላጊ የሆኑትን ምግቦች ለማሟላት የሚያስችል አቅም እና ምቹ ሁኔታ ያለመኖር ብዙ ጊዜ ሕጻናቱ ተገቢውን ጤናማ ምግብ እንዳያገኙ ምክንያት ስለሚሆን በቅርብ የተገኘውን ብቻ አለአግባብ በመመገብ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዲኖራቸው እና ችግር ላይ እንዲወድቁ ምክንያት ይሆናል፡፡  
በተለምዶ የወፈረ ልጅ ጤነኛ ነው የሚል አስተሳሰብ በአንዳንድ አካባቢ በልማድ የሚታወቅ በመሆኑ ወላጆች ከልክ በላይ ልጆቻቸውን እንዲመግቡ ምክንያት መሆኑ ሌላው የህጻናቱን ጤንነት የሚፈታተን ሲሆን በተለይም ተዘጋጅተው ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ እና የስኩዋር እና ጨው እንዲሁም ስብ መጠናቸው ትክክል ያልሆኑ የታሸጉ ምግቦች ከመጠን ላለፈ ውፍረት መንስኤ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥናቶች ይዘግባሉ፡፡  
የህጻናቱን ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለመከላከል የተለያዩ መንገዶች መኖራቸውን የአለም የጤና ድርጅት እንደሚከተለው አስቀምጦታል፡፡
ሀገራት ከመጠን ያለፈ የጨቅላዎች እንዲሁም ህጻናት ውፍረትን ለመከላከል ቀላል የሚሆን ላቸው በመጀመሪያ ይህንን ለማስወገድ የሚ ረዱ ንድፈ ሀሳቦች መቅረጽ ሲቻል እና የመኖሪያ አካባቢን ማስተካከል፤ ትምህርት ቤቶችና የአካ ባቢው ህብረተሰብ የወላጆችን እና የህጻናቱን ፍላጎት እና ምርጫቸውን ማወቅ ሲችሉ ነው። በተጨማሪም ሕጻናቱ ጤናማ ምግብ እንዲያገኙ አቅምን እና ምቹ ሁኔ ታን ማመጣጠን የሚችሉበትን መንገድ እና ጤናማ ምግብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለማወቅ የሚያስችል መረጃን በተገቢው መስጠት ሲቻል ሕጻናቱን ሲወለዱ ጀምሮ ሊገጥማ ቸው የሚችለውን ከመጠን ያለፈ ውፍረት መከላከል ያስችላል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት ለጨቅላ ሕጻናትና ለህጸናት የሚከተለውን ጤናማ አመጋገብ ይመክራል፡፡
ሕጻኑ እንደተወለደ በአንድ ሰአት ጊዜ ውስጥ ጡት ማጥባት፤
ሕጻኑ ከተወለደ ጀምሮ እስከ 6/ወር ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻ እብዲመገብ ማድረግ፤
ሕጻኑ ከተወለደ ከ6 ወር ጀምሮ እስከ ሁለት አመት ድረስ የእናት ጡት ወተት ሳይቋረጥ ተጨ ማሪ ጤናማ ምግቦችን በማዘጋጀት ሕጻኑን መመገብ ያስፈልጋል፡፡ ተጨማሪ ምግቦች ምን እንደ ሆኑ ከባለሙያዎች ምክር መጠየቅ ተገቢ ሲሆን መጠኑንም አነስ አድርጎ በመጀመር እየዋለ እያደር መጨመር እንደሚቻልና ምናልባትም ልጁ ከሁለት አመት በሁዋላም ጡት መጥባት የሚያስችለው ሁኔታ ካለ መከልከል እንደግዴታ የሚቀመጥ አለመሆኑንም መረጃው ይጠቁ ማል፡፡
እድሜያቸው ከጨቅላነት የዘለለው ሕጻናት ምግቦቻቸው የተለያዩ ማለትም ስጋ፤ እን ቁላል፤ አሳ የመሳሰሉትን ሊጨምር እንደሚችል መረጃው ይጠቁማል፡፡ በማንኛውም ሕጻን ምግብ ውስጥ ስኩዋር፤ ጨው እና ስብ ከመጠን ባለፈ መልኩ መጨመር ግን አይገባም፡፡
የአለም የጤና ድርጅት በ2004 እንደውጭው አቆጣጠር ባደረገው አለምአቀፍ ስብሰባ የተመጣ ጠነ ምግብን ለህጻናት በማቅረብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሚመለከት በአለም ያሉ ሀገራት አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ከስምምነት መደረሱን ይህ ዘገባ ያስረዳል፡፡ በመቀጠልም በ2011 በተደረገው የተባበሩት መንግስታት በተደረገው ስብሰባም ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን በመቀነስ ወይንም በማስወገድና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን በሚመለከትም ሀገራት አስፈላጊውን ንድፈሀሳብ በመቅረጽ ፖሊሲ በማውጣት ለተግባራዊነቱም እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ረገድ ኃላፊ ነት እንዲወስዱ የሚያስችል ስምምነት ተደርጎአል፡፡ስለዚህም በ2012 በተደረገው አለምአቀፍ የጤና ስብሰባ ሀገራት የህጻናቱን ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን በሀገራቸው እንዲተገብሩ ከስምምነት ደርሰዋል፡፡
በውጭው አቆጣጠር በ2025 እንዲደረስበት የሚፈለገው የአመጋገብ ስልት የጨቅላ ሕጻናትን የህጻናትንና የእናቶችን ጤና በመጠበቁ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተረጋገጠ ስለሆነ ሀገራት እርምጃ ለመውሰድ ከመስማማታቸውም በላይ ለተግባራዊነቱም እየተንቀሳቀሱ መገኘታ ቸውን የአለም የጤና ድርጅት በ2017/ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡  

Read 2945 times