Saturday, 13 October 2018 10:25

የተስፋዬ ገሰሰ “አስብና ክበር” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(6 votes)

 በናፖሊዮን ሂል “Think and Grow Rich” በሚል ርዕስ የተፃፈው የስኬታማነት ሳይንስ መፅሐፍ በተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ “አስብና ክበር” በሚል አዛማጅና ነፃ ትርጉም፣ ወደ አማርኛ ተመልሶ ለንባብ በቃ፡፡  ከሞተ 50 ዓመታትን ያስቆጠረው ደራሲ ናፖሊዮን ሂል፣ የስኬታማነት ሳይንስ ወይም ስነ - ስኬት ስራ እስካሁንም እንደሚሰራና ወደፊትም መስራቱን እንደማያቆም እርግጠኛ መሆናቸውን የጠቆሙት ተርጓሚው፤ አሁን ያለውን ትውልድ ያስተምራል በሚል እምነት ከእንግሊዝኛ ወደ አማርኛ ተርጉመው ለንባብ ማብቃታቸውን አመልክተዋል፡፡
 የደራሲው የስኬታማነት ሳይንስ እንደሚሰራ በብዙዎች ዘንድ የተመሰከረለት በመሆኑ፣ በመላው ዓለም በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችና በ20ኛው ምዕተ ዓመት የነበሩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት እንደተጠቀሙበት፣አሁንም መፅሐፉን በማንበብ ስኬታማ መሆን እንደሚቻል ረዳት ፕሮፌሰሩ ያስረዳሉ፡፡ በ124 ገጾች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ ፕሮፌሰር ተስፋዬ፤ ከዚህ ቀደም ከ10 በላይ ልቦለዶች፣ የግጥም መድብሎች፣ የኦማር ካያም ሩቢያቶችንና ሌሎች መፅሐፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡   

Read 5942 times Last modified on Saturday, 13 October 2018 12:10