Saturday, 13 October 2018 10:24

ከ”ያ ትውልድ” እስከ “ኢትዮጵያ ሆይ” መፅሐፎች ላይ ውይይት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፍ የሰለጠኑ ተማሪዎች ዛሬ ይመረቃሉ

    ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ከ “ያ ትውልድ” እስከ “ኢትዮጵያ ሆይ” በተሰኙት የክፍሉ ታደሰ መፅሀፍት ላይ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ፣ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ  ውይይት ያካሂዳል፡፡ ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ የሚያቀርቡት የፊልም ባለሙያው አቶ ይድነቃቸው አይኔ ሲሆኑ መድረኩ በሰለሞን ተሰማ ጂ ይመራል ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል፤ሚዩዚክ ሜይ ዴይ ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት ያህል በተለያዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ማለትም፡- በቴአትር፣ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በዘመናዊ ዳንስና በሙዚቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች፣ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት እንደሚያስመርቅ አስታውቋል፡፡  

Read 4745 times