Saturday, 13 October 2018 09:25

ሲኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የጡት ካንሰር ምርመራ ሊያደርግ ነው

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(5 votes)


    ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣውና የበርካታ ዜጎችን ሕይወት እየቀጠፈ ያለውን የካንሰር ሕመም ለመከላከል ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል ተገቢ ነው ያለው ሲኤምሲ አጠቃላይ
ሆስፒታል በኅብረተሰቡ ዘንድ ስለ በሽታው ግንዛቤ መፍጠር እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
ከተመሰረተ 18 ዓመታትን ያስቀጠረው ሆስፒታሉ፣ የጡት ካንሰርን አደገኛነት ለማስገንዘብ እየሰራ ከመሆኑም በላይ ከጥቅምት 5-17 ቀን 2011 በዘመናዊ መሳሪያ (Mamography) በመታገዝ ዕድሜአቸው ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች ነፃ የጡት ካንሰር ቅድመ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ የጡት ካንሰር፣ መደበኛ የጡት ሴሎች ከቁጥጥር ውጭ በመሆን መልኩ በሚበዙበትና ጤናማ አካልን በሚወርሩበት ጊዜ የሚፈጠር ሲሆን፣ በበለፀጉት አገሮች ከ8 ሴቶች አንዷ በጡት ካንሰር የተያዘች እንደሆና ሴቶች በካንሰር የመያዝ ዕድላቸው 150 እጥፍ እንደሆነ ሆስፒታሉ ገልጿል። የጡት ካንሰር ምልክቶች፤ በጡት ላይ እብጠት ወይም ዕጢ፣ የጡት መጠን መጨመር ወይም መቀነስ፣ የጡት ቆዳ መሰርጎድ፣ መቁሰል፣ የጡት ላይ ህመም ሲሆኑ፣ በጡት ላይ የሚታዩ ምልክቶች ሁሉ የካንሰር ምልክቶች ናቸው ማለት እንደማይቻል ተነግሯል፡፡
ማንኛዋም ከ40 ዓመት በላይ የሆናት ሴት በዓመት አንድ ጊዜና በቤተሰብ በሽታው ያለባቸው ከ20 ዓመት ጀምሮ በየሦስት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ (ማሞግራፊ) ማድረግ
እንዳለባቸው መክሯል፡፡

Read 5856 times