Saturday, 06 October 2018 11:15

የኤርሚያስ ለገሰ “ጥላሁን ያረፈ ቀን” ለአንባቢያን ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 የቀድሞ የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የ”ኢሳት” ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተንታኝና ፕሮግራም አዘጋጅ በሆኑት አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተጻፈው “ጥላሁን ያረፈ ቀን” የተሰኘ መጽሐፍ በሳምንቱ መገባደጃ ላይ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
በ310 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ182 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ከመፅሐፉ ገቢ ግማሹ፣ ለበርካታ ዓመታት በእስር ለቆየው ፖለቲከኛ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)፣ የህክምና ወጪ እንደሚውል ለማወቅ ተችሏል፡፡ ደራሲው የመፅሐፉን መታሰቢያነት ለክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ አድርጓል፡፡
 አቶ ኤርሚያስ ለገሰ፤ ከዚህ ቀደም “ባለቤት አልባ ከተማ” እና “የመለስ ልቃቂት” የተሰኙ አገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚዳስሱ መጻሕፍትን ለአንባቢያን ማድረሳቸው ይታወሳል፡፡ 

Read 7561 times