Saturday, 06 October 2018 11:04

6ኛው አግሮ ፉድና ፓኬጂንግ ኤግዚቢሽን በሚቀጥለው ሳምንት ይከፈታል

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

 ኢትኤል አድቨርታይዚንግና ኮሙኒኬሽን ከቱርኩ ግዙፍ ዓለም አቀፍ የኤግዚቢሽንና ጉባኤ አዘጋጅ ኩባንያ ከላዲን ጋር በመተባበር፣ አዲስ አግሮ ፉድ የግብርና፣ የግብርና መሳሪያዎች፣ የምግብ ቴክኖሎጂዎችና የፓኬጂንግ ኤግዚቢሽን ለ6ኛ ጊዜ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2011 በሚሊኒየም አዳራሽ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ከትናንት በስቲያ በሳፋየር ሆቴል በሰጠው መግለጫ፤ በኤግዚቢሽኑ 30 ኩባንያዎች ከሕንድ፣ ከቱርክና ከታንዛኒያ የሚሳተፉ ሲሆን የግብርና መሳሪያዎች፣ የምግብ ማቀነባበሪያ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ እንዲሁም የረቀቁና በዓለም የታወቁ የቡና፣ የፍራፍሬ፣ የጣፋጮችና የመሳሰሉትን የማቀነባበሪያና የፓኬጂንግ ቴክኖሎጂዎችን ለአገራችን እንደሚያስተዋውቅ ተገልጿል፡፡

Read 1856 times