Saturday, 06 October 2018 10:59

የመጀመሪያው አዲስ ፓወር ኤግዚቢሽን ሊካሄድ ነው

Written by  መንግስቱ አበበ
Rate this item
(0 votes)

 ኢትኤል አድቨርታይዚንግና ኮሙኒኬሽን ከቱርኩ የንግድ ትርዒት አዘጋጅ ኩባንያ ቲ.ጂ ኤክስፖ ጋር በመጣመር፣ የመጀመሪያውን አዲስ ፓወር ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ፣ የኤሌክትሮኒክና ላይቲንግ ኤግዚቢሽን፤ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2011 በኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ ያሉ ባለድርሻ አካላትን የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን በሚሌኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
ከትናንት በስቲያ በሳፋየር ሆቴል በተሰጠው መግለጫ፤ በአገራችን እስካሁን ድረስ 29 ሚሊዮን ደንበኞች ከኃይል ጋር መተሳሰራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የኃይል መሰረተ ልማትም የኢትዮጵያን 60 በመቶ ቆዳ እንደሚሸፍን፣ ነገር ግን ቀጥታ ተጠቃሚነቱ 25 በመቶ ብቻ በመሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከኢነርጂ እንደራቁ አመልክቷል፡፡
በዚህ ኤግዚቢሽን 17 የውጭ ኩባንያዎች የሚሳተፉ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢነርጂ ዘርፍ ያለውን ያልተነካ እምቅ አቅም ታሳቢ በማድረግ በርካታ የግሉም ሆነ የመንግስት ባለድርሻ አካላት በኤግዚቢሽኑ እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

Read 1840 times