Print this page
Saturday, 06 October 2018 10:56

የጤና ባለሙያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፎረም…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


    ሕብረተሰብን በማገልገል ረገድ ይህ ሙያ ከዚህኛው ይበልጣል ወይንም ይሻላል አለዚያም ይህን ካገኘሁ ይህ ይቅርብኝ የማይባልበት እና ሁሉም እንደየባህርይው አስፈላጊ ስለሆነ በትክክለኛው መንገድ ህብረተሰቡን የሚጠቅም እንዲሆን ለማድረግ ሩቅ ለሩቅ ሆኖ ሳይሆን በጋራ ክፉና ደጉን ተነጋግሮ እዚህ ጎደለ እዚህ ጥሩ ነው በሚል ቢሆን የበለጠ ተመራጭ  መሆኑን ነበር ከሰሞኑ የተደረገ ስብሰባ ያረጋገጠው፡፡  
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከጥበብ ባለሙያዎች ጋር በቅርብ በጥምረት በመሆን ለመስራት የሚያ ስችለውን ፎረም ለመፍጠር መስከረም 22/2011/ በአዲስ አበባ ከሁለቱም ማለትም ከጤናውና ጥበብ ዘርፉ ተሳታፊዎችን በመጋበዝ ምክክር ባደረገበት ወቅት የተጠቀሰው ጤናማና አምራች ዜጋን ከመፍጠር አኩዋያ ከጤናው ዘርፍ ባልተናነሰ ከጥበብ ዘርፉ የሚጠበቅ አስተዋጽኦ መኖ ሩን እና በአገራችን በጤናው ዘርፍ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣ ጠር ረገድ እንዲሁም በዘርፉ ለተመዘገቡ ስኬታማ ውጤቶች ማህበራቱ ጉልህ ሚና የነበራቸው መሆናቸው ተገልጾአል፡፡ የጥበብና የሙያ ማህበራቱ ይህንን ተግባር ሲሰሩ የመቆየታቸውን ያህል በሌላ በኩል ደግሞ የሚነሱ ጉዳዮችን በተቆራረጠና ባልተሟላ ሁኔታ የማስተላለፍ፤ የጤና ሙያንና የሙያተኛውን ስብእና የሚያጎድፉ ስራዎች የማቅረብ እንዲሁም በበቂ መረጃ ላይ ሳይመረኮዙ የአንድ ወገንን ሀሳብ ብቻ የማንጸባረቅ ሁኔታ አልፎ አልፎ ይስተዋላል፡፡  
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የመረጃ ጉድለትን ለማረምና እና የጤና ሙያ ማህበራቱ በጤናው ሴክተር ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት ይረዳ ዘንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በተዋረድ ያሉ ሴክተር ተቋማትና ተጠሪ ተቋማት ከጥበብ ሙያ ማህበራት በቅርብ የሚገናኙበት የጋራ ፎረም መመስረት አስፈላጊ መሆኑን እና ይህ መድረክም የጋራ ሀሳብን የያዘ እንደሚሆን ተገልጾአል፡፡
የዚህ ጥምረት ዋና ግብ የኪነ ጥበብ ማህበራትን ሙያተኞችንና የጤና ሙያ ማህበራት በጤናው ሴክተር ላይ የሚኖራቸውን የጋራ ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስ ችላቸውን ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ህብረተሰባችን ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃ እንዲያገኝ ማድረግ ነው፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በወቅቱ ካቀረባቸው ቁምነገሮች መካከል የጥምረቱ መፈጠር ዋነኛ አላማ ይገኝበታል፡፡ አቶ ዮርዳኖስ አስባቸው ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባቀረቡት ጽሁፍ እንደተገለጸው፡-
የጥበብ ማህበራት ሙያተኞችንና ያለባቸውን ክፍተት በመለየት በጤናው ዘርፍ ያለውን ጉዳይ በተገቢው ሁኔታ ለመረዳት የሚያስችላቸውን ተከታታይ ስልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
የኪነ ጥበብ ማህበራትንና ሙያተኞች በጤናው ሴክተር የሚከናወኑ ተግባራትን ለመከታተልና የመረጃ ምንጮችን ለማግኘት ያሉትን ችግሮች በጋራ ለመፍታት መድረኩን ይጠቀማሉ፤
የጥበብ ማህበራትን ሙያተኞችን በጤናው ሴክተር ያላቸውን ተሳትፎ በማጎልበት ህብረ ተሰቡ ማግኘት የሚገባውን አዝናኝና ትምህርታዊ መረጃዎችን መስጠት እንዲችል ማገዝ፤
የጥበብ ማህበራትን፤ ሙያተኞችን እና በጤና ሙያ ማህበራቶች በኩል ያለውን ጉዳይ ለኀብረተሰቡ በማድረስ በኩል ያላቸውን የእርስ በእርስ ተሞክሮ መለዋወጥ የሚያስችላ ቸውን መድረክ እንዲፈጠር ማገዝ፤
ተከታታይ የጤና ስራዎችን መስራት እንዲያስችላቸው በመረጃ ምንጭ፤በፋይናንስም ሆነ አስፈላጊ በሆኑ አቅጣጫዎች አቅም ማጎልበት የሚቻልበትን መንገድ በጋራ ለመፍጠር፤
የጥበብ ማህበራትን ሙያተኞችን በጤና ጉዳዮች ላይ ተከታታይነት ያለውና ለለውጥ የሚያበቃ ስራ በማቅረብ በጤናው ዘርፍ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት አካል በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማገዝ፤ የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ይህንን ተግባር እውን በማድረጉ ረገድ ከተጠቀሱት አካላት ውስጥ የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አንዱ ሲሆን የክልል ጤና ቢሮዎችና የጤና ሙያ ማህበራት እንዲሁም የጥበብ ሙያ ማህበራት ይገኙበታል። ህብረተሰቡን በማገልገሉ ረገድ ጉልህ ሚና ያለውን የህክምና ሙያና ሐኪሞችን በሚመለከት በመገናኛ ብዙሀን የሚቀርቡ ዘገባዎች ፊልሞች የሚጻፉ ድርሰቶች …ወዘተ በትክክለኛው መንገድ መሰራት አለባቸው ሲባልም እውነታውን መደበቅ ወይንም ጥፋትን መሸፈን ሳይሆን በትክክለኛው መንገድ ሁሉም ባመኑበት መንገድ መግለጽ ግን ከጥበብ እና መገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች እንደሚጠበቅ በስብሰባው ላይ ጠንከር ብሎ ሀሳብ ተሰንዝሮበታል፡፡ ስለሆነም ይህ ፎረም ስራ ሲጀምር የሚመራባቸው መርሆዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
…ሚዛናዊነትን መጠበቅ፤ የሰዎችን ልእልና አለመንካትን ማረጋገጥ፤ አሳታፊነት፤ ፍትሀዊነት፤ ብዝሀነትንና ግላዊነትን መረዳት፤ ታማኝነት፤ የህዝብ አገልጋይነት፤ የግለሰቦችንና የአካባቢ ሁኔታን ግምት ውስጥ ማስገባት፤ ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት …ወዘተ የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን ቁምነገር እውን ለማድረግ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሚጠበቁት ድርሻዎች መካከል አበባላቱ ዘንድ በጤናው ዘርፍ ላይ በሙያተኞች ዘንድ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ስልጠና ዎችንና ልዩ ልዩ መድረኮችን ማመቻቸት ይጠበቅበታል፡፡ በተጨማሪም በአገሪቱ በጤናው ዘርፍ ልማት የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውረው ለመቃኘት ልዩ ልዩ ስራዎችን ለማዘጋጀት እንዲ ችሉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በተለይም በፎረሙ አባላት አማካኝነት በጤናው ዘርፍ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ የጥበብ ስራዎችን የማየት፤ ከአቀራረባቸው ባሻገር በይዘታቸው በጤና ሙያተኞች እና በህብረተሰቡ መካከል የአለመተማመን ስሜትን የሚፈጥሩ ስራዎችን የመመ ርመር እንዲሁም የሚሻሻሉበትን መንገድ የመፈለግ ድርሻንም ይይዛል፡፡
ፎረሙን በመመስረት በኩል ዋነኛ ድርሻ ካላቸው ውስጥ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ይገኙበታል፡፡ የእነርሱም ተግባርና ኃላፊነት፤
ከጤናው ሴክተር የሚመነጩትን መረጃዎች የማግኘትና የሙያዊ ስነምግባርን በተከተለ መንገድ ለህብረተሰቡ የማቅረብ፤
በአገሪቱ በጤናው ዘርፍ ልማት የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውረው የመቃኘትና የማወቅ ኃላፊነት…ወዘተ አለባቸው፡፡
ህብረተሰቡን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን ማለትም በፊልም በመጽሐፍ በጋዜጣና ሬድዮ እንዲ ሁም ቴሌቪዥን …ወዘተ የተሳሳተ እና የተጋነነ መረጃ ከማቀበል ይልቅ ሙያዊ ስነምግባር በሚጠይቀው መሰረት የተስተካከለ እና ሚዛናዊ የሆነ መረጃን እንዲያቀርቡ ለማስቻል የተለያዩ የጤና ሙያ ማህበራት ድርሻም ፎረሙን ለመመስረት በተጠራው ስብሰባ ላይ ተጠቅሶአል፡፡
የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለጥበብ ባለሙያዎች የመስጠት ኃላፊነት፤
በጥበብ ባለሙያዎች አማካኝነት በጤናው ዘርፍ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ጤና ነክ ይዘት ያላቸውን የጥበብ ስራዎችን የማየት፤ ከአቀራረባቸው ባሻገር በይዘታቸው በጤና ሙያተኞች እና በህብረተሰቡ መካከል የአለመተማመን ስሜትን የሚፈጥሩ ስራዎችን የመመርመር እንዲሁም የሚሻሻሉበትን መንገድ መፈለግ፤
የፎረሙን ዓላማዎች ለማሳካት የሚያግዙ የሀብትና የሎጀስቲክ ትብብሮች እንዲኖሩ የማድረግ እና ሚዛናዊ የሆነ መረጃ የማስተላለፍ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
ይህ የፎረም ምስረታ ስብሰባ የተጠናቀቀውም የጥበብ ባለሙያዎችና የጤና ባለሙያዎቹ ለሁለት ተከፍለው የየራሳቸውን ተወካይ አቅርበው ሲሆን በወደፊቱ አሰራር የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅ ተገልጾአል፡፡

Read 2005 times