Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 11:02

41ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለተተኪዎች ዋና መድረክ ሆነ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

አዲስ አበባና ሶማሌ ያልተሳተፉበት 41ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ነገ ሊፈፀም ነው፡፡ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚዘጋጀው ሻምፒዮናው በአዲስ አበባ ስታዲየም ባለፈው ረቡዕ የተጀመረ ሲሆን ፡ በኦሎምፒክ የሚኒማ ማሟያ ውድድሮች ተሳትፎ ምክንያት ታላላቅ አትሌቶችን ብዙም ባይኖሩበትም በወጣትና ተተኪ አትሌቶችን በብዛት በማሳተፍ  ደማቅ ፉክክር ታይቶብታል፡፡ የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው በኢትዮጵያ የሳምሰንግ ወኪል በሆነው የጋራድ ኩባንያ በ700 ሺ ብር ስፖንሰር መደረጉ ታውቋል፡፡ 41ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስፖንሰሮች የትልልቅ አትሌቶችን ተሳትፎ አለመኖር፤ ስፖርቱን ከስር መሰረቱ ለመደገፍ በሚጎሏቸው ትብብሮች፤ እና የገቢ ምንጮች ባለመኖራቸው ብዙም አጥጋቢ አይደለም፡፡

በየስፖንሰር እጥረት ሳቢያ ውድድሮችን በቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት ለማስተላለፍ አልተቻለም ምናልባት ነገ የፍፃሜ ውድድሮች ስርጭት ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በየውድድሮቹ ለሚያሸንፉ አትሌቶች የሚሰጠው ሽልማትም አንሷል፡፡ ይሁንና የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ሃላፊዎች በሰጡት መግለጫ ሻምፒዮናው በ5ሺሜ፤ በ3ሺ መሰናክልና በሌሎች ውድድሮች እስክ 3 ማጣርያዎች ለማለፍ በብዛት አትሌቶች መኖራቸው፤ በሜዳ ላይ የተለያዩ ስፖርቶች በቴክኒክ የተሻለ ተሳትፎ ሊያሳዩ መጠበቁና የክልሎች ተሳትፎ መጠናከር አበረታች ሆኗል፡፡ አሸናፊ አትሌቶች በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለሚሳተፉ ቡድኖእች የመመረጥ እድላቸው ሰፊ መሆኑ ትልቁ ኽልማት ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በቀጣይ ዓመት ብሄራዊ የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው በስፖንሰሮች ድጋፍ ተጠናክሮ፣ በሽልማት አድጎ፤ የቀጥታ ቴሌቭዥን ስርጭት ኖሮትና ለመጀመርያ ግዜ የመስተንግዶ አቅም ባላቸው ክልሎች እንዲዘጋጅ ጥረት መደረጉ እንደሚቀጥል ይገልፃል፡፡የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣  የአዲስ አበባ አስተዳደር ለክልልና ለክለብ በሚሰለፉ ተጨዋቾች ውዝግብ ከተሳትፎ መቅረቱን ሲገልፅ ሁኔታው በቀጣይ እንዳይደገም ምክክር ላይ መሆኑን አሳውቋል፡፡ በሌላ በኩል የሱማሌ ክልል ባለው የአስተዳደር ግንኙነት አለመቀላጠፍ መሳተፍ አለመቻሉንም እየመረመረ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ የድሬዳዋ አስተዳደርን ጨምሮ ከተቀሩት 8 ክልሎችና 19 ክለቦች ወንዶች 513፣ ሴቶች 483 በድምሩ 996 አትሌቶች  በያዙባቸው ቡድኖች  እየተሳተፉበት ናቸው፡፡ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ ውርወራና ዝላይን ጨምሮ ከአጭር ርቀት እስከ አሥር ሺሕ ሜትር ያሉትን ያጠቃልላል፡፡ ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶች ለማፍራትና ዓለም አቀፍ የውድድር ዕድል የማያገኙ አትሌቶች ምቹ መድረክ መሆኑን የገለፁት የፌደሬሽኑ ሃላፊዎች በመጪው ክረምት በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው የመጀመርያው የዓለም ወጣቶች ሻምፒዮናና በቤኒን በሚስተናገደው 18ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደረጃ ውስጥ የሚገቡ አትሌቶች የመጀመርያ ተመራጭ ይሆናሉ፡፡በሌላ በኩል ውርወራና ዝላይን ጨምሮ የአጭር ርቀት ተወዳዳሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ውጤት ባይኖራቸውም በቀጣይ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚሆኑ አትሌቶችን ከምልመላ ጀምሮ ለይቶ በማውጣት ፌዴሬሽኑ በዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

Read 2539 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 11:06