Monday, 10 September 2018 00:00

ለአዲስ ዓመት ዋዜማ የት እንሂድ?

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የዘንድሮ አዲስ ዓመት ለየት ያለ ነው፡፡ በአገሪቱ ላይ በመጣው ለውጥ የተነሳ የዜጎችም መንፈስና ስሜት ተለውጧል፡፡ የነጻነት አየር እየነፈሰ ይመስላል፡፡ ይሄን ተከትሎም ለአዲሱ ዓመት በርካታ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ይመስላል፡፡ በዚህ ልዩ ወቅት ታዲያ ዋዜማውን የት እናሳልፍ? ለሚሉ ውድ አንባቢያን፤የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፣ በከተማዋ የዋዜማ ልዩ ዝግጅት ያሰናዱ ሆቴሎችን አስሳ፣ የጥቂቶቹን መረጃ እንዲህ አጠናቅራለች፡፡ መልካም ዋዜማ!!
መልካም አዲስ ዓመት!


     የዘንድሮ አዲስ ዓመት ለየት ያለ ነው፡፡ በአገሪቱ ላይ በመጣው ለውጥ የተነሳ የዜጎችም መንፈስና ስሜት ተለውጧል፡፡ የነጻነት አየር እየነፈሰ ይመስላል፡፡ ይሄን ተከትሎም ለአዲሱ ዓመት በርካታ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው ገብተዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ይመስላል፡፡ በዚህ ልዩ ወቅት ታዲያ ዋዜማውን የት እናሳልፍ? ለሚሉ ውድ አንባቢያን፤የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ፣ በከተማዋ የዋዜማ ልዩ ዝግጅት ያሰናዱ ሆቴሎችን አስሳ፣ የጥቂቶቹን መረጃ እንዲህ አጠናቅራለች፡፡ መልካም ዋዜማ!! መልካም አዲስ ዓመት!
ራማዳ አዲስ ሆቴል - ከድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ጋር
ቦሌ ዋናው መንገድ ላይ የሚገኘው ራማዳ አዲስ ሆቴል፤ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ልዩ የኮክቴልና የቀጥታ የመድረክ ሙዚቃ ዝግጅት በዋዜማው ሰኞ ማታ ያቀርባል - ከነገ ወዲያ ጳጉሜ 6 ቀን 2010 ዓ.ም፡፡ ከምሽቱ 2፡30 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 7፡00 በሚዘልቀው በዚህ ልዩ የእራትና የኮክቴል ምሽት፤ለእንግዶች እራት በቅናሽ የሚቀርብ ሲሆን “ዌልካም ድሪንክን” እና ወይንን ጨምሮ ለአዋቂዎች በ675 ብር፣ ከ5-12 ዓመት ዕድሜ ላሉ ልጆች በ405 ብር መዘጋጀቱንና የ”ባላገሩ አይዶል” አሸናፊው ድምጻ ዳዊት ፅጌ፣ ከግሩቭ አዲስ ባንድ ጋር ምሽቱን እንደሚያደምቀው የሆቴሉ ረዳት ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ዮናስ ፋሲል ተናግረዋል፡፡ በምሽቱ የርችት ማብራት ሥነ-ሥርዓትና ሌሎች መዝናኛዎች እንደተዘጋጁ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሀርመኒ ሆቴል
ቦሌ ከኤድናሞል ዝቅ ብሎ በሚገኘው ሀርመኒ ሆቴል ራስ ባር፣ በዋዜማ ምሽት ልዩ የኮክቴል ዝግጅት የተሰናዳ ሲሆን በዚህ ዝግጅት ላይ ለመታደም ለጥንዶች 899 ብር፣ ለብቸኛ ግለሰብ 499 ብር የመግቢያ ዋጋ ያስከፍላል - ከእራት ጋር፡፡ በምሽቱ በዓል በዓል የሚሸቱ የተመረጡ ሙዚቃዎች በዲጄ የሚቀርቡ ሲሆን የዋዜማው ዝግጅት ከምሽቱ 1፡00 እስከ እኩለ ሌሊት እንደሚዘልቅ የሆቴሉ የገበያ ጥናት ባለሙያ አቶ አላዛር ግርማ አስታውቀዋል፡፡  
ኢዮሃ አዲስ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንት
በአዲሱ ዓመት ዋዜማ፣ሰኞ ጳጉሜ 6 ቀን 2010 ዓ.ም ኢዮሃ አዲስ ኢንተርቴይንመንትና ኤቨንት በመስቀል አደባባይ የሙዚቃ ኮንሰርት ያቀርባል፡፡ በዚህ የዋዜማ ኮንሰርት ላይ ታዋቂና ስመ ጥር አቀንቃኞች በመሀሪ ብራዘርስ ባንድ ታጅበው ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን ከነዚህም መካከል ድምፃዊ ዘለቀ ገሰሰ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ተመስገን ገ/እግዚአብሔር፣ አቡሽ ዘለቀ፣ ሰለሞን ኃይለ፣ ሮፍናን እና ብስራት ሱራፌል እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8፡00 እንደሚዘልቅ በተነገረለት በዚህ ኮንሰርት፤ የአዲስ ዓመት አብሳሪ ርችት እንደሚተኮስ የጠቆመው አዘጋጁ፤ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ነው ብሏል፡፡  
ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል
ካዛንቺስ የሚገኘው ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቪአይፒ ሬስቶራንቱ ልዩ የአዲስ ዓመት ዋዜማ እራት አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ የእራት ምሽት የተመረጡ የዲጄና የፒያኖ ሙዚቃዎች የሚቀርቡ ሲሆን፤ መግቢያ በነፃ መሆኑንና እራት ቢራን ጨምሮ 800 ብር ያስከፍላል ብለዋል - የሆቴሉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ዋሲሁን፡፡ በዋዜማው ልዩ ዝግጅት ላይ አምሽተው፣ አዳራቸውን እዚያው ለሚያደርጉ ዳያስፖራዎች፤በመኝታ ክፍሎች ዋጋ ላይ የ25 በመቶ ቅናሽ እንደሚደረግም ለማወቅ ተችሏል፡፡  
ራዲሰን ብሉ ሆቴል
ካዛንቺስ የሚገኘው ባለ 5 ኮከቡ ራዲሰን ብሉ ሆቴል እንዲሁ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ልዩ የእራት ምሽት አዘጋጅቷል፡፡ የእንኳን ደህና መጣችሁ መጠጥ፣ ወይን በብርጭቆ፣ ልዩ የቡፌ እራትና አይረሴ የፎቶ ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል፡፡ “አሮጌውን ዓመት እንሸኘው፤ አዲሱን እንቀበለው” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ልዩ ምሽት ላይ ለመታደም፣ በሰው 999 ብር ያስከፍላል፡፡       

Read 4787 times