Print this page
Monday, 10 September 2018 00:00

በህዳሴ ግድብ ግንባታ ምዝበራ የፈፀሙ ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(11 votes)


     ከህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት አፈፃፀም ጋር ተያይዞ “ስለተፈፀመው ከፍተኛ ዘረፋ” ለህዝብ ማብራሪያ እንዲሰጥ የጠየቀው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፤ በዘረፋውና ምዝበራው የተሳተፉ የመንግስት ኃላፊዎች በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል፡፡
ለሃገሪቱ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ዘርፍ ብዙ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለተደራጀ ዘረፋ ተጋልጦ እንደነበር ከቀረቡ ዘገባዎች መረዳት መቻሉን የጠቆመው አብን፤ መንግስት የፕሮጀክቱ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ዝርዝር መረጃ መስጠት እንዳለበት ገልጿል፡፡
በግድቡ ግንባታ ወቅት መጓተትን የፈጠሩ፣ በህዝብ ሃብትና ገንዘብ ምዝበራ የተሳተፉ እንዲሁም ምዝበራው ሲፈፀም ማስቆም ሲገባቸው ያላስቆሙ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች ተጠያቂ እንዲደረጉ ንቅናቄው ጠይቋል፡፡
በቀጣይም ግልፅ የፋይናንስ ሥርዓት ተዘርግቶ፣ ግንባታው በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ መደረግ አለበት ብሏል አብን ባወጣው መግለጫው፡፡
የግድቡን የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታ ኮንትራት የወሰደው ሜቴክ፤ ስራውን በአግባቡ ባለማከናወኑ “ለኪሳራ ተዳርጌያለሁ” ያለው የሲቪል ግንባታ ኮንትራክተሩ ሳሊኒ መንግስትን 3.5 ቢሊዮን ብር እና 338 ሚሊዮን ዩሮ መጠየቁ ይታወቃል፡፡

Read 10692 times