Monday, 10 September 2018 00:00

“ሰተቴ” የአንድ ሰው ትያትር ለዕይታ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


    የጅማው ምፀተኛ ባለቅኔ፣ከድር መሃመድ፤ በብዙዎች ዘንድ በሰላ ንግግሮቹና  አስገራሚ ድርጊቶቹ የሚታወቅ የእውነትና የ መብት ተሟጋች ነው። ከ1941-1981 ዓ.ም እንደኖረ የሚነገርለት ከድር፤ በአካባቢው ህዝብ “ሰተቴ” በሚል ቅፅል ስም ይጠራል፡፡ ጅማ ጮጬ ተወልዶ፣ በጅማና አጋሮ ኖሯል፡፡ በፖለቲካ ሂሶቹ ብቻ ሳይሆን  ማህበራዊ ጉዳዮችንም በመተቸት ይታወቃል - ከድር መሃመድ፡፡
“ ኢሰፓኮ ባዶ ፓኮ...”
“ጥይት ነው ጋኔኑ ተብለው ሲያበቁ
ባሩዱን ደብቀው ቀለሃ አጠመቁ።” ...በሚሉና በሌሎችም ቅኔዎቹ፤ ሲታሰር ሲፈታ የኖረ ሲሆን  መጨረሻው የጥይት ሲሳይ ሆኗል፡፡ በስሙ ሁለት መፅሐፍት ተፅፈው ለንባብ በቅተዋል - በተስፋዬ አየለ “ሽንቁርና ውታፍ” እንዲሁም በዲርዓዝ ፣”ሰተቴ” ናቸው፡፡  
“ሰተቴ” የተሰኘው የአንድ ሰው ትያትር፤ባለፈው  ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጅማ ዶሎሎ ሲኒማ ቤት የተመረቀ ሲሆን ትያትሩ በተስፋዬ አየለ ፀሐፊነትና አዘጋጅነት እንዲሁም በቁሜ አዱኛ ተዋናይነት ለእይታ መብቃቱ ታውቋል፡፡  የ1:40 የመድረክ ቆይታ ያለው ትያትሩ፤ በቀጣይም በመላው ኢትዮጵያ ለተመልካች ይቀርባል ተብሏል፡፡

Read 1014 times