Tuesday, 04 September 2018 09:32

ግብጽ በአፍሪካ ረጅሙን ህንጻ ልትገነባ ነው

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ግብጽ በአፍሪካ በቁመቱ ቀዳሚ እንደሚሆን የተነገረለትንና የናይል ማማ የሚል ስያሜ የሰጠቺውን ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በመዲናዋ ካይሮ፣ ከአባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ በ600 ሚሊዮን ዶላር ልትገነባ መሆኑን ፎርብስ ዘግቧል፡፡
የዚህ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ፕሮጀክት የተወጠነው ከአስር አመታት በፊት በቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ የስልጣን ዘመን እንደነበረ ያስታወሰው ዘገባው፣ በ2011 በተቀሰቀሰው አብዮት ሳቢያ ፕሮጀክቱ ተቋርጦ መቆየቱንና በወቅቱ መሪ አብዱልፈታህ አልሲሲ ፈቃድ እንዲቀጥል መደረጉንም አመልክቷል፡፡
ዛሃ ሃዲድ በተባሉት ታዋቂ የአገሪቱ አርክቴክት ከ11 አመታት በፊት ንድፉ ተሰርቶ የተጠናቀቀው ህንጻው፣ 70 ወለሎች እንደሚኖሩት የጠቆመው ዘገባው፣ 36 ወለሎች ለአፓርትመንት፣ 18 ወለሎች ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን፣  የተቀሩት ወለሎች ደግሞ የገበያ ማዕከል፣ የመዝናኛ ስፍራ፣ የምሽት ክለብና ለሌሎች በርካታ ጥቅሞች እንደሚውሉ አስረድቷል፡፡

Read 1633 times