ዘጠነኛው ዙር ሰምና ወርቅ የኪነ ጥበብ ምሽት በልዩ የበዓል ፕሮግራም ዝግጅት የፊታችን ሐሙስ በቫምዳስ የመዝናኛ ማዕከል ከ11፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ ዶ/ር ብርሃኑ ግዛው፣ አርቲስት አዜብ ወርቁ፣ ወግ አዋቂው በኃይሉ ገ/መድኅን፣ አንጋፋዋ ብዕረኛ መቅደስ ጀምበሩ፣ ገጣሚዎቹ ኤፍሬም ስዩም፣ ትዕግስት ዓለምነህ፣ የሺመቤት ካሳ፣ መምህርት እፀገነት ከበደና በቅርቡ ከአሜሪካ የመጡት አርቲስት ተክሌ ደስታና ደራሲና ጋዜጠኛ አለማየሁ ገ/ህይወት ተገኝተው ምሽቱን እንደሚያደምቁት ታውቋል፡፡ የኪነ ጥበብ ዝግጅቱ መሶብ ባህላዊ ባንድ እንደሚታጀብም የሰምና ወርቅ የኪነ ጥበብ ምሽት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው አለሙ ገልጿል፡፡