Print this page
Saturday, 01 September 2018 15:33

የ“አዲስ ሚዩዚክ አዋርድ” ምርጥ አምስቶች ታወቁ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

 የዘጠነኛው የ“አዲስ ሚዩዚክ አዋርድ” ምርጥ አምስት እጩዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በዚህም መሰረት፤ የዓመቱ ምርጥ አልበም ውስጥ የናቲ ማን “የመጀመሪያ ነው”፣ የሮፍናን “ነፀብራቅ”፣ የብስራት ሱራፌል “ቃል በቃል”፣ የሄለን በርሄ “እስኪ ልየው” እና የእሱ ባለው ይታየው “ትርታዬ” ያለፉ ሲሆን፣ በየዓመቱ ምርጥ ቪዲዮ ዘርፍ፡- የቴዎድሮስ ካሳሁን “ማር እስከጧፍ”፣ የስካት ናቲ “ስራ”፣ የአበበ ከፈኒ “አና ሲወያ”፣ የሳሚ ዳን “ሀያል” እና የአሌክስ “ወገቧ” ምርጥ አምስት ውስጥ ገብተዋል፡፡ በምርጥ ሙዚቃ አቀናባሪ ዘርፍ፡- ካሙዙ ካሳ፣ ጊልዶ ካሳ፣ ስማገኘሁ ሳሙኤል፣ ሮፍናንና ታምሩ አማረ ሲያልፉ፣ በየዓመቱ ምርጥ ተዋናይት ዘርፍ ደግሞ እፀ ህይወት አበበ በ “አስነኪኝ”፣ አዚዛ አህመድ በ “ትህትና”፣ ሰላም ተስፋዬ በ “ያበደች ያራዳ ልጅ”፣ ዮአዳን ኤፍሬም በ“አብሳላት” እና አዲስአለም ጌታነህ በ “ሀ እና ለ 2” ታጭተዋል፡፡
የዓመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ በተሰኘው ዘርፍ ሰለሞን ሀይለ በ “ደስ ይበለኖ”፣ ያሬድ ነጉ በ“ዘለላ”፣ ዝናር ዜማ በ “የኔ ሴት”፣ ስካት ናቲ በ “ስራ” እና ብስራት ሱራፌል በ“የቤት ስራ” ሲያልፉ፣ የዓመቱ ምርጥ ድምፃዊ፡- ሮፍናን፣ እሱባለው ይታየው፣ ሀብታሙ ገ/ፃዲቅ፣ ዲጄሊ እና አበባው አበበ ምርጥ አምስት ውስጥ ገብተዋል፡፡ በዓመቱ ምርጥ ፊልምም “ያበደች ያራዳ ልጅ”፣ “ትህትና”፣ “አፄ ማንዴላ”፣ “በእናት መንገድ” እና “ድንግሉ” እና “ዘናጭ” በእኩል ነጥብ ምርጦቹ አምስት ውስጥ ተቀላቅለዋል። የዓመቱ ምርጥ ተዋናይ ዘርፍ ውስጥ ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) በ“አስነኪኝ”፣ ዓለምሰገድ ተስፋዬ በ “ያበደች ያራዳ ልጅ”፣ ካሳሁን ፍስሃ (ማንዴላ) በ“ዘናጭ”፣ ዓለማየሁ ታደሰ በ “ድንግሉ” እና ሰለሞን ቦጋለ በ “አብሳላት” እጩ መሆናቸውን የአዲስ ሚዩዚክ አዋርድ ዋና አዘጋጅ ይግረም ስንታየሁ (ዲጄ ቤቢ) አስታውቋል፡፡

Read 6014 times