Print this page
Saturday, 01 September 2018 15:32

“ቃል ሜሞሪ” የተማሪዎችን የመዝጊያ ውድድር ዛሬ ያካሂዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “ቃል ሜሞሪ” የማስታወስ ጥበብና ሁለንተናዊ የአዕምሮ እድገት ስልጠና ማዕከል፤ በማስታወስና ሂሳብን በአዕምሮ ብቻ ካልኩሌተር ፈጥሮ የማስላት ስልጠና ሲያወዳድራቸው የነበሩ ተማሪዎችን ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማንዴላ አዳራሽ የመጨረሻዎቹን 200 አሸናፊ ተማሪዎች ይፋ ያደርጋል፡፡ እስከ ዛሬ ሲወዳደሩ የነበሩት ከ48 ት/ቤቶች የተውጣጡና እድሜያቸው ከ5-13 ዓመት የሆኑ 1502 ተማሪዎች እንደነበሩ የገለፀው የስልጠና ማዕከሉ፤ በዛሬው ዕለት ምጡቅ አዕምሮ ያላቸውን 200 ተማሪዎች ለመለየት ውድድሩ እንደሚካሄድና አሸናፊዎችን እንደሚሸልም ታውቋል፡፡
 የማስታወስ ጥበብና ሁለንተናዊ የአዕምሮ እድገት ስልጠና ለሁለተኛ ዙር የተካሄደ ሲሆን የመጀመሪያው በስኬት እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 839 times