Saturday, 01 September 2018 15:30

በመምህር ገላውዴዎስ አለልኝ የተዘጋጀው “ፈረንሳይኛ ቋንቋን ያለአስተማሪ” መፅሐፍ ሰሞኑን ለገበያ ቀርቧል፡፡ አዘጋጁ መፅሀፉን ያሰናዱበትን ምክንያት ሲገልፅ፤ “ይህንን መፅሐፍ ለመፃፍ ሳስብ የኔ መፅሐፍ ከሌሎች መፃህፍቶች በተለይ መንገድ እውቀትን ያካፍላል ብዬ ሳይሆን በተለይ አማርኛ ለሚያነቡ ምንም ሳይቸገሩ በቀጥታ ወደ ንግግርና ንባብ ይመራቸዋል በሚል እሳቤ መሆኑ ይታወቅልኝ” ብሏል በመግ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


    በሁለት ኢትዮጵያውያንና በሁለት እንግሊዛዊያን በ2006 ዓ.ም የተመሰረተው ራኬኤሌ የፋሺን ዲዛይን ኮሌጅ፤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከፍለው መማር ለማይችሉ 30 ያህል ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠቱን አስታወቀ፡፡ ት/ቤቱ በፋሽን ዲዘይን በንድ፣ በማሽን ጥገናና በዘርፉ ተያያዥነት ባላቸው ሙያዎች ከመሰረታዊ ስልጠና ጀምሮ ከደረጃ 1-4 ስልጠናዎች ሲያስመርቅ እንደቆየ ከኮሌጁ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ሀዱሽ ስዩም ተናግረዋል፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ኮሌጁ በአገራችን እያደገ የመጣውን የፋሽን የጋርመንት ዘርፍ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ክፍተት ለመሙላት የበኩሉን እያደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ነፃ የትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን ተናግረዋል፡፡ በተገባደደው 2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም ለ27 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል መስጠታቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ት/ቤቱ እስከዛሬ ከ420 በላይ ሰልጣኞችን አስተምሮ ወደ ሥራ እንዲቀላቀሉ ማድረጉን እንዲሁም ሰሞኑንም 210 ያህል ሰልጣኞችን ለማስመረቅ መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

Read 747 times