Saturday, 01 September 2018 15:27

“ምስጢረ ፊደል” ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 ደራሲ፣ ጋዜጠኛና የባህል ተመራማሪ መምህር ካሕሳይ ገ/እግዚአብሔር ያዘጋጁት “ምስጢረ ፊደል ወትርጓሜሁ” (የፊደል ምስጢር ከእነ ትርጉሙ) የተሰኘ መፅሐፍ ሰሞኑን ለገበያ ቀረበ፡፡
“ምስጢረ ፊደል፤ የግዕዝ ቋንቋና ፊደል ለሀገራችን ሥነ ፅሁፍ ባህል፣ ትውፊትና ታሪክ መሰረትና ምንጭ ብቻ ሳይሆን የጥንታዊ ሥልጣኔያችን መሰረት … እንዲሁም የግዕዝ ፊደል የራሱ ትርጉምና ምስጢር ያለው መሆኑን የሚያሳይና በውስጡ ለጥናትና ምርምር መነሻ የሚሆኑ አዳዲስ መረጃዎችን ያካተተ ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በትክክለኛ የሆሄያት አፃፃፍ መሰረት መፃፍ ለሚፈልጉ ፀሐፍት፣ ደራሲያን፣ ተማሪዎች በመረጃ ምንጭነት የሚያገለግል ጭምር ነው” ብለዋል ደራሲው - ስለ መፅሐፉ በላኩት አጭር ሃተታ፡፡ “ምስጢረ ፊደል” ለደራሲ ካሕሳይ ሰባተኛ መፅሐፋቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም “የኃብር ብዕር መፅሐፍ” (ከ1ኛ መፅሐፍ እስከ 3ኛ መፅሐፍ)፣ “ምንኩሳን በኢትዮጵያ”፣ “ብፅዓን እነማን ናቸው” እና “ባህልና ክርስቲያናዊ ትውፊት በኢትዮጵያ” የሚሉ መፃህፍትን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡ በ292 ገፆች የተቀነበበው “ምሥጢረ ፊደል”፤ በ110 ብር ይሸጣል፡፡

Read 1445 times