Print this page
Saturday, 01 September 2018 15:14

100 ሺ ብር መደለያ የቀረበላቸው ፖሊሶች ህገወጦችን በቁጥጥር ስር አዋሉ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(8 votes)

ከጥቁር ገበያ ጋር በተያያዘ የታሸጉ ሱቆችን በመክፈት የውጪ አገር ገንዘቦችን ለማውጣት በማሰብ 100 ሺ ብር ለፖሊሶች መደለያ ያቀረቡት ግለሰብና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
በከተማዋ የውጪ አገር ገንዘቦች በህገ ወጥ መንገድ ከሚመነዘርባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው ጋንዲ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኙት የንግድ ሱቆች መካከል ጥቂቶቹ ከዚሁ ተግባር ጋር በተያያዘ ሰሞኑን እንዲታሸጉ ተደርገዋል፡፡ ሱቆቹ ከመታሸጋቸውም ሌላ በፖሊስ ኃይል ሲጠበቁና ቁጥጥር ሲደረግባቸው ቆይቷል፡፡
ባለፈው ረቡዕ አመሻሽ ላይ ከታሸጉት የንግድ ሱቆች መካከል የአንደኛው ሱቅ ባለቤቶች ሥፍራውን ከሚቆጣጠሩት የፖሊስ አባላት መካከል ለሁለቱ “100 ሺ ብር ጉቦ እንስጣችሁና ሱቁን ከፍተን በውስጡ የሚገኘውን ገንዘብ እናውጣ” የሚል ጥያቄ ያቀርቡላቸዋል፡፡ የፖሊስ አባላቱም በሃሳቡ የተስማሙ በመምሰል የሱቁን ባለቤትና ተባባሪዎቻቸውን በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሲሆን፤ ሱቁ ተከፍቶ ፍተሻ ሲደረግም ከ300 ሺ ብር በላይ እና በ10 ሺዎች የሚቆጠር የውጪ አገራት ገንዘብ ተይዟል፡፡ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

Read 14833 times