Tuesday, 28 August 2018 00:00

“ደቂቀ ኢትየጵያ” መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ ዮሴፍ አባይ የተፃፈው “ደቂቀ ኢትዮጵያ” ረጅም ልቦለድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መፅሐፉ በዋናነት በስደት ህይወትና ፈተናዎቹ ላይ የሚያተኩር ሲሆን መቼቱን ዱባይና ኢትዮጵያ እንዳደረገ ለማወቅ ተችሏል “… ከሀገር ውጭ ባለኝ ቆይታ የኖርኩትን፣ ያየሁትን፣ ያሰላሰልኩትን፤ የሰማሁትን በስነ ፅሑፍ ለመግለፅ እንዲሁም የስደትን ጭንቀት፣ መከራ፣ ምኞትት ሀሳብ፣ ኑሮና ውስጤን በብዕር የቀለም ጠብታ ለመግለፅ ሞክሬያለሁ…” ሲል ደራሲው ታሪኩ በእውነተኛ የህይወት ተሞክሮ ላይ ተሞርኩዞ መፃፉን በመግቢያው ላይ አስፍሯል፡፡ በ15 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ234 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ በ100 ብር፣ በ20 ዩሮ እና በ20 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 3821 times