Saturday, 12 May 2012 09:23

ደራስያን በእናት ማስታወቂያ ተሸለሙ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ከመስከረም 2003 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2003 ዓመተምህረት ታትመው ለንባብ የበቁ የረዥም ልቦለድ፣ የአጭር ልቦለድ እና የሕፃናት መፃሕፍት ተወዳድረው ተሸለሙ፡፡ እናት የማስታወቂያ ሥራዎች ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ፀደይ ወንድሙ፣ ደረጄ ገብሬ፣ አለማየሁ ገላጋይ፣ አስቻለው ከበደ እና ዮናስ ታረቀኝ በዳኝነት መርተውታል፡፡ የዛሬ ሳምንት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመፃሕፍት እና ቤተመዛግብት አዳራሽ በተከናወነ ሥነ ሥርአት የአዳም ረታ “ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ”፣ የእነዬ ሺበሺ “የገቦ ፍሬ”፣ የድርቡ አደራ “ሽንብሩት” በረጅም ልቦለድ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ወጥተዋል፡፡

በድርጅቱ መረጃ በተጠቀሰው ጊዜ የወጡት የአጭር ልቦለድ ስብስቦች ሁለት ብቻ በመሆናቸው የአባተ ማንደፍሮ “የደም ምድር” እና የአንተነህ ይግዛው “መልስ አዳኝ” ልዩ ተሸላሚ ሲሆኑ በሕፃናት መፃሕፍት ዘርፍ ረዳት ፕሮፌሰር ዓለም እሸቱ በሌሉበት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የረዥም ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ደራሲና ሃያሲ አስፋው ዳምጤ ሲሸለሙ የኢትዮጰያ ደራስያን ማህበርና የኢትዮጵያ ሴት ደራስያን ማህበር ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ተሸላሚዎቹ በትዕዛዝ የተቀረፀ የክሪስታል ዋንጫ ከክብር እንግዳው ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ እጅ ተቀብለዋል፡፡

 

 

 

Read 1560 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:25