Saturday, 18 August 2018 09:25

“የሀገረሰብ አስተዳደር፣ የህግና የፍትህ ሥርዓቶች በኢትዮጵያ” ሰኞ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በአራት የኢትዮጵያ ክፍሎችና በመሀል ኢትዮጵያ በተለይም በሸዋ ግዛት ስለነበረውና አሁንም ጥቅም ላይ ስለሚውለው አገር በቀል የሀገረሰብ አስተዳደርና የፍትህ ሥርዓቶች ላይ የሚያጠነጥነው የደራሲ አብዱልፈታህ አብደላህ “የሀገረሰብ አስተዳደር፣ የህግና ፍትህ ሥርዓት በኢትዮጵያ” መፅሐፍ ሰኞ ከቀኑ 11፡00 ይመረቃል፡፡ መፅሐፉ የየአካባቢዎችን ባህል፣ አለባበስ አስተዳደርና የፍትህ ሥርዓቶች በፎቶግራፍ አስደግፎ የሚተነትን ነው፡፡ በ271 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ በ169 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
በእለቱ ዲስኩር፣ ጭውውት አነቃቂ ንግግሮችና ግጥም ይቀርባል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችን ባህል፣ ወግና ማንነት የሚገልፁ መፅሐፍትንና ማውጫዎችን በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡

Read 733 times