Saturday, 18 August 2018 09:22

የማህጸንና ጽንስ ሕክምና የስነ ምግባር መመሪያ…

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)


    ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሕክምናው አለም የተለያዩ ሳይንሳዊ እድገቶች የተመዘገቡ ሲሆን ምንም እንኩዋን በሚፈለገው ደረጃም ማለትም የተጠቃሚውን ቁጥር ከግምት ውስጥ ያስገባ ባይሆንም የባለሙያዎቹም ቁጥርም እየጨመረ መሆኑ አይካድም፡፡ የመድሀኒቶች አይነት መጨመር የቴክ ኖሎጂ መስፋፋት …በተለይም በማህጸንና ጽንስ ሕክምናው ዘርፍ በሰዎች ሕይወት ዙሪያ ያሉትን ነገሮች ከመረዳት ፤ልጅ ከማዋለድ፤ የስነ ተዋልዶ ጤና፤እድሜ እና ሞት የመሳሰሉት በሕክምናው አለም ልዩ ትኩረትን የሚሹ በመሆናቸው በአገልግሎት ሰጪው እና ተገልጋዩ መካከል ያለውን ግንኙነት ያወሳስበዋል፡፡ በዚህ መሀል የህክምናው ባለሙያ አንዳንድ ጊዜ ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል የሚለውን ለመወሰን የሚያሽቸግሩት ነገሮች ቢገጥሙት ሊመራበት የሚገባ የስነ ምግባር መመሪያ ያስፈ ልጋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ህክምና ባለሙያዎች የስነምግባር መመሪያ አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበትም የኢትዮጵያ የማህ ጸንና ጽንስ ሕክምና ባለሙያዎች ማህበር ከአሜሪካው የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ሰነዱ በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡ ይህ የስነምግባር መመሪያ በመጪው የESOG አመታዊ ጉባኤ ላይ ቀርቦ በጠቅላላው ጉባኤ ይጸድ ቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዶክተር ሙኒር ካሳ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስት እንዲሁም በኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የሙያ ስነምግባር ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡እሳቸው እንደሚሉትም
ሕክምናን ለመስጠት ህብረተሰቡ በሕክምናው ላይ እምነት ሊያሳድር ወይንም እምነት ሊኖረው ይገባዋል፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ለስራቸው የሚመሩበትን ሕግ ወይንም የስነምግባር መመሪያ ምንነት ለህብረተሰቡ ማሳወቅ እና እነሱም አውቀው እንዲያከብሩ በማድረግ በዚያ መሰረት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የማህጸን እና ጽንስ ሐኪሞች ለሕመምተኛው መደረግ ያለበት የትኛው ነው ?የሚለውን ለመወሰን የሕመም ተኛው ፈቃድ፤ የሚኖረው አቅም የመሳሰሉት ሁሉ የሚያስፈልጉ ሲሆን ይህንን በትክክ ለኛው መን ገድ ለመምራት የሚያስችል የስነ ምግባር መመሪያ ነው በመዘጋጀት ላይ ያለው ፡፡ ይህንን የስነም ግባር መመሪያ ለማውጣት በማህጸንና ጽንስ ሕክምና ማህበር አንድ ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በአጠቃላይም የማህጸን ሕክምና ባለሙ ያዎቹ ገጠመኞች ፤ ሀሳቦች፤ አዳዲስ እውቀቶች ፤የስራ ልምዶች የመሳሰሉት አስፈላጊ በመሆና ቸው ሰነዱን ሙሉ ለማድረግ በስብሰባ ውይይት ይደረ ጋል፡፡ ውይይቱ በተለያዩ መስተዳድሮች ለአራት ጊዜ የሚ ደረግ ሲሆን የመጀመሪያው በአዲስ አበባ በውጭው አቆጣጠር August 6-7/ ተካሂዶ አል፡፡ በስብ ሰባ ውም ላይ ከተነሱት ልምዶች እና ለመፍታት አስቸጋሪ ከነበሩት መካከል የሚከተሉትን ዶ/ር ሙኒር አስታ ውሰዋል፡፡
‹‹…ከአንድ ሆስፒታል የቀረበ አንድ ጉዳይ እንደሚከተለው ነው፡፡ አንዲት ሴት የዘጠኝ ወር እርጉዝ ሆና ወደሆስፒል ትመጣለች፡፡ በጊዜው ሜኔንጃይትስ በተባለው በሽታ ምክንያት የአእ ምሮ ኢንፌ ክሽን ያጋጠማት ሲሆን በፍጥነት ወደ ህክምናው ባለመምጣትዋም ምክንያት አእምሮዋ ከጥቅም ውጭ ሆኖአል፡፡ እርጉዝዋ ሴት ትተነፍሳለች እንጂ አእምሮዋ ሞቶአል፡፡ ያረገዘችው ልጅ ግን በሕይወት ስላለ ኦክስጂን እየተሰጣት ልጁን መቆጣጠር ነበር የሐኪሞቹ ስራ፡፡ ይህች ሴት እርጉዝ ባትሆን ኖሮ ሞታለች የምትባል ነች፡፡ መናገር ፤ማየት፤ ማሰብ የሚባል ነገር አቁማ ለች፡፡ ልጁ ግን በሕይወት ስለአለ ምን እናድርግ የሚለውን ለመ ወሰንም እስዋን ለማማከር አልተቻለም፡፡ባልተቤትዋም አልቀረበም፡፡ ስለዚህ ለቤተሰብዋ ልጁን በኦፕ ራሲዮን እናዋ ልደው ተብሎ ቢነገራቸው አልተ ስማሙም፡፡ ምክንያቱም እኛ አቅም ስለሌለን በፍጹም ልጁን ማሳደግ አንችልም …ስለዚህ አንፈልገውም የሚል ነበር መልሳቸው፡፡ በስተመ ጨረሻ ሐኪሞቹ በኮሚቴ ልጁን ለማሳደጊያ ለመስጠት ወስነው እና ይህንኑ ለቤተሰብ አስረድ ተው በመወለዱ ህይወቱ እንዲተርፍ ተደረገ፡፡ እንደዚህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የግድ የስነምግባር መመሪያው አስፈላጊ ይሆናል፡፡ምክንያቱም ፈቃዳቸውን መስጠት የሚችሉት ታካ ሚዎች መፍቀድ ወይንም መከልከል በማይችሉበት ወቅት አንድ ሐኪም ብቻውን ሊያደርግ የሚችለው ነገር ስለሌለ በመሐከል ሕይወት አለአግባቡ እንዳይጠፋ ለማድረግ ነው፡፡ ››
‹‹…ሌላው ጉዳይ….አንዲት ሴት የእርግዝና ምርመራ ለማድረግ ወደሆስፒታል ትመጣለች፡፡ በደምዋ ውስጥም ኤችአይቪ ቫይረስ መኖሩ ሲረጋገጥ ይነገራትና በቀጣይም ባለቤትሽን ይዘሽ ነይ ስትባል…. አ.አ.ይ…እኔ አልናገርም… ይህን ከነገርኩት ይፈታኛል የሚል መልስ ትሰ ጣለች፡፡ አንድ ሐኪም ደግሞ የታካሚውን ምስጢር መጠበቅ ግዴታው ነው፡፡ ነገር ግን ባልየው ከቫይረሱ ነጻ ቢሆን እንኩዋን ዝም ከተባለ በሂደት ሊያጋጥመው የሚችለው ነገር አይታወቅም፡፡ ማንኛውም ምስጢር ከታካሚዋ ፈቃድ በስተቀር ለማንም አይነገርም የሚል አሰራር ባለበት እንደዚህ ያለውን ችግር ለመፍታት የግድ የስነምግባር መመሪያው ያስፈልጋል፡፡ ››
የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር በማዘጋጀት ላይ ያለው የስነምግባር መመሪያ የሚያስቀ ምጣቸው አሰራሮች አሉ፡፡ ለምሳሌም ታካሚዋ ፈቃድ መስጠት ወይንም መከልከል በማትች ልበት ወቅት ጉዳዩ ይበልጥ ለባልተቤትዋ ወይንም ለቤተሰብዋ ጎጂ የሚሆን ከሆነ ምን ሊደረግ ይገባል የሚለውን ለመወሰን መመሪያው ያግዛል፡፡ ታካሚዋ በጤና ችግር ምክንያት ፈቃድዋን መስጠት በማትችልበት ጊዜ ደግሞ የቤተሰብ ውሳኔ ተቀባ ይነት የሚኖረው ታካሚዋን የመጀ መሪያ ምርጫቸው አድርገው ሲቀርቡ ነው፡፡ ለምሳሌም እናትየው የምትፈልገው እንደዚህ ቢሆን ነው ሲሉ ነው እንጂ ከእኛ ጥቅም አንጻር ይህ መደረግ የለበትም ቢሉ ተሰሚነት አይኖረ ውም፡፡ የታካሚውን ምስጢር በመጠበቅ ረገድ አንድ ሐኪም በምንም ምክንያት የአንዱን ጉዳይ ለሌላው አይናገርም ሲባል ሚስት ስለባልዋ ፤ባልም ስለሚስቱ እንዲሁም እናትና አባት ስለልጃ ቸው ወይ ንም ልጅ ስለእናት አባቱ ጤንነት ሁኔታ እና ሌሎችም በጎን ሄደው ሐኪም ቢጠይቁ ምንም መረጃ  ከሐ ኪሙ ማግኘት አይችሉም ማለት ነው፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሕክምና የስነምግባር መመሪያ በዋናነት አራት ክፍሎች አሉት፡፡
1/ የታካሚውና የሐኪሙ ግንኙነት፤
አንድ ሐኪም ከበሽተኛው ጋር በሚኖረው ግንኙነት ዋናው ማጠንጠኛ የበሽተኛዋ ፍላጎት፤ ነጻነት፤ ውሳኔ ነው፡፡ ታካሚዋ ስለጤናዋ በሚገባ አውቃ የምትወስነውን ነገር ሐኪሙ ያከብራል፡፡ሐኪሞች የታካሚዎቻቸውን መብት የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው፡፡
የታካሚዋ ደህንነት ወይንም ጤነኛነት ለታካሚውና ለሐኪሙ ግንኙነት ወሳኝ የሆነ ወይንም ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡
የህግ መመሪያው በእድሜ፤ በጋብቻ፤ በዘር፤ በሀይማኖት፤ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚ፤ በአካል ጉዳተኝነት በመሳሰሉት ሁሉ ሰዎችን ማንገላታት ወይንም ተገቢውን ክብር አለመስጠትን ይቃወማል፡፡
በተቻለ መጠን በማንኛውም መንገድ የጥቅም ግጭትን  ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡
2/የሐኪሙ ጸባይ፤
የማህጸንና ጽንስ ሐኪም በባህርይው ከሕመምተኞችም ጋር ይሁን ከስራ ባልደረቦቹ ጋር የተስማማ መሆን አለበት፡፡
የማህጸን ሐኪሙ አንዲትን ሴት በማከም ረገድ ያለውን የሙያ ብቃት እና የአገልግሎት ጥራት ደረጃ በጠበቀ መንገድ ያሉትን የህክምና መገልገያዎች በመጠቀም በጊዜው ያለ ውን አስፈላጊ ሕክምና እንዲሰጥ ይጠበቃል፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሐኪም ከታካሚያቸው፤ ከቤተሰብ፤ ከስራ ጉዋደኞች፤ ከተማሪዎች፤ ከአዋላጅ ነርሶች እና ከሌሎቹም ባለሙያዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት ሊኖረው ይገባል፡፡
3/ይህ ሐኪም ከሌሎች ሀኪሞች ጋር ያለው ግንኙነት፤
የማህጸንና ጽንስ ሐኪም ከሌሎች የህክምና ባለሙያዎች ጋር ባለው ግንኙነት ጥሩ ተባባሪ እና ለሙያው ግምት የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡
4/ሐኪሙ ከማህበረሰቡ ጋራ የሚኖረው ግንኙነት፤
ማንኛውም ሐኪም የሚሰራው ስራ ሙያውን በሚያስከብር መልኩ መሆን አለበት፡፡ ለማህበረ ሰቡ በተለይም ሴቶችን የሚያግዝ ስራ ላይ መሳተፍም ይጠበቅበታል፡፡ ሴቶች የስነተዋልዶ ጤና ቸውን ለመጠበቅ የሚያስችላቸው አቅም በየተቋማቱ እንዲጎለብት የሚያስችል ብር እንዲመደብ ጭምር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር ወይንም ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገር ይጠበቅበታል፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ የስነተ ዋልዶ ጤናዋን ችግር በሚመለከት በቅርብ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሙ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ለምሳሌም…የማህጸን ካንሰር ፤የጡት ካንሰር የመሳሰሉት ሕመሞች ሕክምና ሊያገኙ የሚችሉባቸውን መንገ ዶች ማመቻቸት፤ የጾታ ጥቃትን ለመከላከል መንገዶቹን ማመላ ከትና ለዚያም የሚያስ ፈልገውን መፍትሔ መጠቆም ከማህጸንና ጽንስ ሐኪሙ  ይጠበቃል፡፡

Read 364 times