Sunday, 12 August 2018 00:00

ከ50 በላይ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የጋራ የእርቀ ሠላም ጉባኤ ሐሙስ ይካሄዳል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

በቅርቡ ወደ ሃገር ውስጥ የተመለሡትን የፖለቲካ ድርጅቶች ጨምሮ ከ65 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሣተፉበት ሁሉን አቀፍ የብሄራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ የፊታችን ሐሙስ በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ስለ ብሄራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም የሚመክሩበት ነው የተባለለት ይሄው ጉባኤ፤ ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2010 በራስ ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልፃል፡፡
በዚህ ጉባኤ ላይ በሃገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ በለውጡ ጀማሮና ቀጣይነት፣ እንዲሁም በሃገሪቱ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ዘላቂ እልባት በሚያገኘበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስተባባሪዎቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
በተመሣሣይ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ሚዲያዎች፣ የሲቪክስ ተቀማትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ የብሄራዊ መግባባት የእርቀ ሠላም ጉባኤ እንደሚካሄድም አስተባባሪ ኮሚቴው ጨምሮ ገልጿል፡፡
የጉባኤው ዋና አስተባባሪዎች “ሠማያዊ ፓርቲ”፣ “ኢዴፓ”፣ “መኢአድ”፣ “የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት” እና “ኢራፓ” መሆናቸው ታውቋል፡፡


Read 7825 times