Saturday, 11 August 2018 10:46

“መቆያ 1” እና “እሪ በከንቱ” የግጥም መድበሎች ገበያ ላይ ዋሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


    በገጣሚ መላዕከ ብርሃን አድማሱ የተፃፉና በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ከ110 በላይ ግጥሞችን ያካተተው “መቆያ 1” የግጥም መድበል በገበያ ላይ ዋለ፡፡ በ121 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ በ100 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በቅርቡ እንደሚመረቅም ተነግሯል፡፡
በተመሳሳይ፤ በአዲስ አበባ በልማት ስም እየተነሱ ወደ ጥግ በሚገፉ ነዋሪዎችና በመዲናዋ መቆሸሽ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘው “እሪ በከንቱ” የተሰኘው የገጣሚ ዳንኤል ታረቀኝ የግጥም መድበል ሰሞኑን ለንባብ በቅቷል፡፡
 የ“ሪፖርተር” ጋዜጠኛ ነአምን አሸናፊ በመፅሐፉ ጀርባ ላይ ባሰፈረው አስተያየት፤ “… በዚህ የግጥም መድበል ውስጥ ለአብነት ያህል “ጮኸብኝ ዝምታ”፣ “የኛ ቤት”፣ “ሽንትና አዲስ አበባ”፣ “ዝምታ መልስ ነው”፣ “ወዴት አለሽ ሞራል”፣ “ጉዞ ወደ ሁካታ” እና “የደም ውለታ” የተሰኙት ስነ ልቦናዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ግጥሞች የገጣሚውን ጥልቅ ትዝብት ያንፀባርቃሉ፡፡” ብሏል፡፡ 84 ገፆች ያሉት መድበሉ፤ ዋጋው 46 ብር ከ90 ሳንቲም ነው፡፡

Read 1577 times