Saturday, 12 May 2012 09:06

“ሜን ኢንብላክ 3” በጉጉት እየተጠበቀ ነው

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

“ሜን ኢን ብላክ 3” ከሳምንት በኋላ በመላው ዓለም መታየት እንደሚጀምር “ቫኒቲ ፌር” መፅሄት አስታወቀ፡፡ ለእይታ የሚበቃበት ግዜ በተደጋጋሚ ሲቀያየር የቆየው “ሜን ኢን ብላክ 3” ላይ በመጀመርያዎቹ ሁለት በፊልሙ የተለያዩ ክፍሎች ጣምራ መሪ ተዋናዮች ሆነው የሰሩት ዊል ስሚዝና ቶሚሊ ጆንስን እንዲሁም አዲሱ ባልደረባቸው ጆስ ብሮሊን አስደናቂ  ትወና ማሳየታቸውን የገለፀው መፅሄቱ፤ ታዋቂዎቹ ሙዚቀኞች ጀስቲን ቢበርና ሌዲ ጋጋ በተጋባዥ ተዋናይነት መሳተፋቸው ፊልሙን አጓጊ እንዳደረገው አመልክቷል፡፡ ዊል ስሚዝ በፊልሙ ላይ ለመተወን 20 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈለው መፅሄቱ ሲገልፅ፣ ጥቁር አሜሪካዊው ተዋናይ ሰሞኑን ለፊልሙ ፕሮሞሽን ከመስራቱ ጐን ለጐን ለፕሬዝዳንት ኦባማ ድጋሚ ምርጫ ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

በ3ዲ የተዘጋጀው “ሜን ኢን ብላክ 3” በይዘቱ ሳይንሳዊ ልቦለድ ሲሆን 215 ሚሊዮን ዶላር ወጥቶበታል፡፡ ፊልሙን ዲያሬክት ያደረገው ባሪ ሳንፊልድ ሲሆን ታዋቂው ስቴቨን ስፒልበርግ ደግሞ በፕሮዲውሰርነት ተሳትፎበታል፡፡ የፊልሙ የመጀመርያ ክፍል ከአስራ አምስት ዓመት በፊት በ90 ሚሊዮን ዶላር በጀት ተሰርቶ  ሲታይ በዓለም ዙርያ 590 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን ያመለከተው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ፤ ከአስር ዓመት በፊት በ140 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተሰራው “ሜን ኢን ብላክ 2” ደግሞ በዓለም ዙርያ 442 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደነበረው ይገልፃል፡፡

 

 

 

Read 1375 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:13