Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 12 May 2012 09:05

ማይሊ ሳይረስ በአዲሱ ፊልሟ አልተሳካላትም “ዘ አቬንጀርስ” ሪኮርድ ያዘ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በማይሊ ሳይረስ የተሰራው “ሎል” የተባለ አዲስ ፊልም በገበያ እንዳልተሳካለት “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” አስታወቀ፡፡ ላዮን ጌትስ 11 ሚሊዮን በጀት አውጥቶ የሰራው የማይሊ ሳይረስ ሮማንቲክ ኮሜዲ ፊልም፤ በ2005 እ.ኤ.አ ላይ በፈረንሳይ ከተሰራ ተመሳሳይ ይዘት ካለው ፊልም የተቀዳ ነው ተብሏል፡፡ የ19 ዓመቷ ማይሊ ሳይረስ በከፍተኛ ስሜት በሰራችው በዚህ ፊልሟ ላይ ዴሚ ሙርም እንደተወነች የታወቀ ሲሆን ከተጠበቀው በታች ገቢ ማስገኘቱ ያልተጠበቀ መሆኑን ገልፃል፡፡

“ሎል” በመጀመርያ ሳምንቱ ያስገኘው ገቢ ከ50ሺ ዶላር አይበልጥም፡፡በሌላ በኩል ባለፈው ሳምንት በሰሜን አሜሪካ ለመጀመርያ ግዜ የታየው የሱፐርሂሮዎች ጀብደኛ ፊልም “ዘ አቬንጀርስ” በሰሜን አሜሪካ 200 ሚሊዮን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ አስመዝግቦ፣ አዲስ ሪኮርድ መያዙን ሮይተርስ ገለፀ፡፡ ፊልሙ በሰሜን አሜሪካ ገበያ በመጀመርያ ሳምንት ባስገባው ገቢ ሪኮርዱን የያዘው  ከዓመት በፊት የሃሪ ፖተር የመጨረሻ ክፍል በሰሜን አሜሪካ ያገኘውን የመጀመርያ ሳምንታዊ ገቢ በ30 ሚሊዮን ዶላር በመብለጡ ነው፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች መታየት ከጀመረ ወር ያለፈው “ዘ አቬንጀርስ” በዓለም ዙርያ የሰበሰበው ገቢ 641 ሚሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡

 

 

 

Read 2096 times Last modified on Saturday, 12 May 2012 09:13