Saturday, 28 July 2018 16:10

“ቀዳሚ ቃል” እና “ቀናሁ በጨረቃ 2” ማክሰኞ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በደራሲ ገጣሚና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ልሳኑ የተሰናዱት “ቀዳሚ ቃል” የተሰኘ ራስን ስለማወቅና ስለመፈለግ በማተት ስነ-ምግባር ማጎልበት ላይ የተሰሩ ሀቲቶች የተካተቱበት “ቀዳሚ ቃል” መፅሀፍና “ቀናሁ በጨረቃ 2” እና “የሰንበት ወግ” የግጥምና የወግ ስብስብ መፅኀፍ የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይመረቃሉ መፅሀፎቹን በሆስፒታሉ ለማስመረቅ የታሰበው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሙያዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ባለሙያዎችን ለማመስገንና መፅሀፍት በሆስፒታል ለታካሚዎች የሚደርስበትን ሁኔታ ለማለማመድ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
መፅሐፎቹ በአሜሪካ በ Amazon.com ላይ በ19.99 እና በ20 ዶላር እየተሸጡ እንደሆነና ወደፊት በኢትዮጵያ ለማሳተም ዕቅድ እንዳለ ተገልጿል፡፡ ደራሲ ገጣሚና ጋዜጠኛ ኢሳያስ ልሳኑ በዋሽንግተን፣ በአትላንተና በሳንፍራንሲስኮ የሚሰራጨው “ኢትዮ ዲያስፖራ” ራዲዮ ባልደረባ ሆነው እየሰሩ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3892 times