Saturday, 21 July 2018 13:17

“የግዮን ውርስ” ቴአትር ዛሬ ለተመልካች ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ ያንፀባርቃል ተብሏል

    በደራሲና ዳይሬክተር እሱባለው የኔነህ የተዘጋጀው “የግዮን ውርስ” የተሰኘ የሙሉ ሰዓት ቴአትር፤ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ለተመልካች ይቀርባል፡፡
ቴአትሩ ምንም እንኳ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ላይ ለምርቃት የበቃ ቢሆንም የታሪኩ ዋና ጭብጥ አገራችን በአሁኑ ወቅት ያለችበትን የሰላምና የመረጋጋት፣ በኢትዮ ኤርትራ መንግስታት መካከል የተደረገውን ስምምነትና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያጠናክር በመሆኑ፣ዛሬ በድጋሚ ለእይታ እንደሚበቃ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በቴአትሩ ላይ ዮሊያና ተክሉ፣ አበራ ሃ/ማሪያም፣ ብርሃኑ ማንተጋፍቶት፣ አበበ አሰፋ፣ ህይወት ይሄነው፣ ሶስና አበበ፣ አቤኔዘር አለማየሁና ሌሎችም ይተውኑበታል፡፡ ቴአትሩን፤ቃላይ የቴአትር ዝግጅት ክፍል ከኤዝቤይ ቴአትር ፕሮዳክሽን ጋር በመተባበር እንደሚያቀርብ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 872 times