የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (ኢትዮ ፉስት) ከቫምዳስ የመዝናኛ ማዕከል ጋር በመተባበር፤ “የፊልም ጥበብ ማነቆዎችና የለውጥ እርምጃ” በሚል ርዕስ ሁለተኛውን ዙር ውይይት፤ የዛሬ ሳምንት ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በቫምዳስ መዝናኛ ማዕከል ይካሄዳል፡፡
በውይይቱ ላይ የፊልም ባለሙያዎች፣ የሲኒማ ቤት ተወካዮች፣ ማህበራት፣ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉ ሲሆን ቀደም ሲል በዘርፉ የነበሩ ማነቆዎች አሁን ባለንበት የለውጥ ዘመን እንዴት ይወገዳሉ በሚለው ላይ ጠንከር ያሉ ሃሳቦችና ጥናታዊ ወረቀቶች እንደሚቀርቡ የኢትዮፉስት መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ይርጋሸዋ ተሾመ ገልፀዋል፡፡ የዛሬ ሳምንት በሚካሄደው ውይይት፤ በክፍል አንድ ውይይት ላይ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳቦች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡