Saturday, 14 July 2018 12:28

ዓለም አቀፍ ሞዴል ዮሐንስ አስፋው የ”ፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም” ብራንድ አምባሳደር ሆነ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በ2018 የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ የሚስተር ሞዴል 2018 አሸናፊ በመሆን የወርቅ ዋንጫ አሸናፊ የሆነው ዓለም አቀፍ ሞዴል ዮሐንስ አስፋው፤ የ“ፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም” ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ፡፡
ሞዴል ዮሐንስ፤ ብራንድ አምባሳደር የሆነው “ፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም” ከ10 ዓመት በፊት በከፍተኛ ካፒታል የተቋቋመና ከጣሊያንና ከተለያዩ የአውሮፓ አገራት የሚያስመጣቸውን ደረጃቸውን የጠበቁ ልዩ ልዩ ብራንድ ያላቸው የወንድ አልባሳት የሚሸጥ ድርጅት ነው፡፡
ከትላንት በስቲያ ረፋድ ላይ በሽራር ኢንተርናሽናል ሆቴል ሞዴል ዮሐንስ አስፋው እና ድርጅቱ የሥራ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን “ፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም” ለሞዴል ዮሐንስ ለቀጣዩ 2 ዓመታት የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ እንዲሰራ 300 ሺህ ብር እንደከፈለው ታውቋል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ወጣት ዮሐንስ በኒዮርክና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በርካታ የፋሽን ትርኢቶች ላይ መሳተፉን ገልፆ የአገራችን ድርጅቶች በአገራቸው ሞዴል ምርቶቻቸውን ማስተዋወቃቸው በአገራችን የፋሽን ኢንዲስትሪው እያደገ መምጣቱን ያመላክታል ብሏል፡፡
የፎር ዩ ስታይል ፕላቲኒየም ባለቤት ከሆኑት አንዱ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ አንድዬ ዘርጋው፤ ድርጅታቸው የአገራችንን የፋሽን ኢንዱስትሪ ለማሳደግ የበኩሉን ለመወጣት እየጣረ ለመሆኑ ማሳያው ለወጣቱ ሞዴል ከፍተኛ ክፍያ በመክፈል ለማሰራት መፈራረሙ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡


Read 1966 times