Saturday, 14 July 2018 12:26

ደራሲ አሰፋ ገብረማሪያም ተሰማ ዛሬ ይዘከራል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን ደራሲ አሰፋ ገብረ ማሪያም ተሰማን ዛሬ ጠዋት ከ4፡00 ጀምሮ በብሔራዊ ቤተ መፃህፍትና ቤተ - መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ይዘከራል፡፡
በዚህ የዝክር ሥነ ስርዓት ላይ ተባባሪ ፕ/ር ተስፋዬ ገሰሰ፣ ሠዓሊ እሸቱ ጥሩነህ እና ደራሲ ጌታቸው በለጠ በደራሲው ህይወት ዙሪያ ንግግርና፣ ዝክረ - ሀሳብ እንደሚያቀርቡ ደራሲያን ማህበር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ደራሲ አሰፋ ገብረማሪያም ተሰማ “የመስከረም ጮራ” እና “The voice” የግጥም ስብስቦችን ለንባብ ያበቁ ሲሆን “ጁሊየስ ቄሳር” እና “ዋናው ተቆጣጣሪ” ትያትርን ወደ አማርኛ መተርጎማቸው ይታወቃል፡፡ “ኢትዮጵያ ቅደሚ” የተሰኘው የቀድሞው የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ደራሲም መሆናቸው አይዘነጋም፡፡

Read 1013 times