Saturday, 14 July 2018 12:24

Prostate…ከወሲብ ጋር ያለው ግንኙነት….

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(7 votes)

 አንደኛው በወሲብ ጊዜ ከሚወጣው ከወንድ የዘር ፍሬዎች ጋር አብረው የሚወጡት ፈሳሾች የተወሰነው ድርሻ ከፕሮስቴት (prostate) እጢ ነው፡፡ ይህ ፈሳሽ በዘልማድ ስፐርም ወይንም የወንድ የዘር ፍሬ ቢባልም ትክክለኛው መጠሪያ ግን ሴሚናል (seminal fluid) ነው ሚባለው፡፡ ይህም ማለት በወሲብ ጊዜ የሚወጣው ፈሳሽ ስፐርም ብቻ ሳይሆን ሌላም ተቀላቅሎ የሚወጣ ፈሳሽ አለ፡፡ ከዚህ ፈሳሽ የተወሰነው ክፍል ከፕሮስቴት እጢ ነው ሚመነጨው፡፡
ሌላው የሽንት ፈሳሽ ሲወጣ አካባቢውን በመጭመቅ ፈሳሹን በትክክል እንዲወጣ የማድረግ ስራም አለው ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡
የፕሮስቴት እጢ በሽታው በሚኖርበት ጊዜም ሆነ ኦፕራሲዮን ከተደረገም በኋላ ቢሆን መጠነኛ የሆነ ወሲብ የመፈጸም ችግር ሊያስከትል የሚችል መሆኑ ቢታመንም እደዋነኛ የወሲብ ችግር ግን ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም፡፡ ዋነኛዎቹ የወሲብ ችግሮች ሌሎች ናቸው፡፡ ለመጥቀስ ያህል፡-
የወሲብ ፍላጎት ማነስ፣
premature ejaculation …በወሲብ ጊዜ ሴቷ ሳትዘጋጅ ወንዱም ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርግ ገና ግንኙነት እንደ ተጀመረ ስፐርም ማፍሰስ ማለት ነው፡፡
ሶስተኛው ችግር የወንድ ብልት አስፈላጊ በሆነ ደረጃ ያለመዘጋጀት ነው፡፡
በእርግጥ ከላይ የተጠቀሱት ችግሮች ከሚከሰቱበት ምክንያት አንዱ በፕሮስ ቴት አካባቢ በሚከሰቱ ችግሮች ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ነገር ግን የወንድ ብልት የሚቆመው ተገቢ የሆነ የደም ዝውውር ወደ ብልት ሲሄድ ስለሆነ ችግር የሚሆነው በደምስር (vascular) ምክንያት የሚከሰት ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላው የነርቭ ችግር ሲኖር ነው፡፡ አንድ ሰው በአከርካሪ አጥንት አካባቢ ወይንም ወገቡ ላይ ችግር ካጋጠመው የወሲብ ችግር ሊከሰት ይችላል፡፡ ከፍተኛውን የወሲብ ችግር የሚፈጥረው ደግሞ የስነልቡና (psychologicall) ችግር ሲኖር ነው፡፡ ጭንቀት ሲኖር የወሲብ ችግር ይከሰታል፡፡ እድሜም እየጨመረ ሲሄድ የወሲብ ችግር ሊኖር ይችላል። የወሲብን ችግር የሚያመጡ ሕመሞችም አሉ፡፡ ለምሳሌ… የስኳር በሽታ ፣የደም ግፊት፣የልብ በሽታ፣ የካንሰር በሽታዎች በተለይም prostate ካንሰር የወሲብ ችግር ይፈጠራል፡፡ እንግዲህ በወንዶች ላይ የሚከሰተው የፕሮስቴት ችግር ከወሲብ ጋር በተገናኛ ሁኔታ መጠነኛ ችግር የሚያስከትል ቢሆንም እንደዋነኛ የወሲብ ችግር መንስኤ ተደርጎ የሚቆጠር ግን አይደለም፡፡
አብዛኞቹ ወንዶች በፕሮስቴት እጢ ሕክምና ምክንያት የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ካገኙ በሁዋላ ቀድሞ እንደነበሩበት የወሲብ አቅማቸው በትክክል ላይመለስ ይችላል፡፡ አንዳንድ ወንዶች ምናልባትም ለወሲብ የመዘጋጀት አቅማቸው ቢኖርም በትክክል እንደቀድሞው ላይሆን ይችላል የሚለው ግምት ከራሳቸው ከታካሚዎቹ አንደበት ከሚሰነዘር ሀሳብ መነሻ ያደረገ ነው፡፡  አን ዳንዶች እንዲያውም ከሴት ጋር ለመገናኘት የሚያበቃቸው አካላዊ ዝግጁነት አይታይ ባቸውም፡፡ በአርግጥ እነዚህን ሰዎች ወደትክክለኛው የወሲብ ድርጊት ለመመለስ የሚያ ስችል የተለያዩ የህክምና እርዳታዎች መኖራቸውንና የተቻ ለውን ሁሉ በመሞከር ቢያንስ በአንዱ ተገቢውን እርዳታ ማግኘት እንደሚቻል ባለሙ ያዎች ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን የተወሰኑ ጊዜ ያትን ስለሚወስድ በትእግስት መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ይመክራሉ፡፡  
በአብዛኛው የቀዶ ሕክምናው ጉዳት የሚያደርስበት ምክንያት ከነርቭ ሲስተም ጋር በተገናኘ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ የነርቭ ሲስተሙ እንዲጎዳ ወይንም ተግባሩን እንዲያቋርጥ ስለሚያደርገው መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህ የሚጎዳው ነርቭ በጀርባ በኩል በፕሮስቴት እጢና በአካባቢው ባሉ ክፍሎች ጋር በተያያዘ የሚገናኘው ነው፡፡
ብዙ ወንዶች የፕሮስቴት ካንሰር ሳይጠና ወደሕክምናው ከሄዱ እና በጨረር ወይንም በቀዶ ሕክምና ከተረዱ የሚከሰተው ዘላቂ ችግር ምናልባትም በህክምናው መካከል ብዙም ልዩነት አይታይበትም እንደባለሙያዎቹ አባባል፡፡ ምናልባትም የሚታየው ልዩነት በጨረር የታከሙ በየጊዜው እድሜ በጨመረ ቁጥር የወሲብ ንቃት እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን በቀዶ ሕክምና የታከሙት ግን ወዲያው ሕክምናው እንደተሰጣቸው የወሲብ አቅማቸው ቢቀንስም ቀዶ ሕክምናው ከተደረገ በሁለት አመት ጊዜ ግን እንደቀድሞውም ባይሆንም ግን የመሻሻል ሁኔታ ይስተዋልበታል። በ 4/አራት አመት ጊዜ ውስጥ ግን በሁ ለቱም መንገድ የፕሮስቴት ካንሰር ሕክምና የወሰዱ ወንዶች ተመሳሳይ የጤና ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡ ስለሆነም ወንዶች የፕሮስቴት ሕመምን ከእድሜ አንጻር አስቀ ድሞ ሊዘ ጋጁበትና ወደከፋ ደረጃ ሳይደርስ ሕክምና ሊያደርጉ እንደሚገባ የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

Read 8686 times