Sunday, 06 May 2012 15:12

እንደ ስብሐት

Written by  አልአዛር ኬ.
Rate this item
(0 votes)

ዲስኩርና ሙግት ሳይሆን ሥራ!

በአለማችን ላይ ታትመው እናነባቸው ዘንድ እነሆ በረከት ከተባልነው ተቆጥረው የማያልቁ መጽሐፍት ውስጥ እድሜ ዘመናችንን ሁሉ ስናነበው ብንኖር ረቂቅነቱ የማይጓደልና ሁሌም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብነው ያህል ሆኖ ከሚሰማን ድንቅ መጽሐፍት አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው (ቅዱስ ቁርአንም እንዲሁ)በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታዲያ ለበርካታ ጊዜያት ተደጋግሞ የተገለፀ አንድ አሪፍ ጉዳይ አለ፡፡ ግዜር ሽርካችን ስለሆነ እኛን ባይጠላንም ከሁላችንም አስበልጦ የሚወዳቸውና የመረጥኩት ህዝቤ እያለ የሚጠራቸው ይሁዲዎችን ነው፡፡ እግዜር እነሱን ከሁሉ አስበልጦ ቢወዳቸውና ቢመርጣቸውም እነሱ ግን አንድም ጊዜ የልቡን አድርሰውለትና እርሱ እንደሚፈልገው ሽርኩና ታዛዥ ሆነውለት አያውቁም፡፡ ሙሴ ከግብጽ እየመራ ሲያወጣቸው የሠሩት ስራ ሰውየው ሙሴ ባይሆን ኖሮ፣ በዚያ በረሃ ጣጥሏቸው የትሜናው በሄደ ነበር፡፡ እግዜር በተራቡ ጊዜ ከሠማይ መናን አውርዶ ከመገባቸው በኋላ ትንሽ ሲጠግቡ እግዜርን እንሸውደው ተባብለው ጣኦት ማምለካቸውን ጀምረው ነበር፡፡

ያኔ ታዲያ በዚህ የማይገባ ድርጊታቸው የተቆጣው እግዜር፤ ለምን ይሄን ድርጊት ፈፀማችሁ እያለ ከነሱ ጋር አንዳችም ክርክርና ሙግት ሳይገጥም የሚገባቸውን ቅጣት በተግባር እየቀጣ ያሳያቸው ነበር - ማረን አጥፍተናል እስኪሉ ድረስ፡፡ ይሁዲዎቹ ከዚያ ትምህርት ወስደው ነው መሠል በክርክርና በተግባር ማሳየትን በተመለከተ በየአጋጣሚው ሁሉ የሚናገሯት አንድ አሪፍ አባባል አላቸው፡፡ ነገርየዋ እንዲህ የምትል ናት:- “በክርክርና በሙግት ተገኘ የሚባል ጊዜአዊ ድል አክሳሪ ድል ነው፡፡ ክርክሩና ሙግት ካስገኘው ድል ይልቅ የሚፈጥረው የቅሬታና የመከፋት ስሜት ከድሉ ስሜትና ከሌላ የሃሳብ ለውጥ የበለጠ ለረጅም ጊዜ በሰዎች ልብ ውስጥ ይኖራል፡፡”የይሁዲ አባቶች ልጆቻቸውን፤ “ሰዎች ከእናንተ ሃሳብ ጋር እንዲስማሙ ከፈለጋችሁ በክርክርና በሙግት ለማሳመን ከመጣጣር ይልቅ ሠርቶ በተግባር ማሳየት የበለጠ የማሳመን ሃይል አለው፡፡” እያሉ አጥብቀው ይመክሯቸዋል፡፡ እነዚህ የይሁዲ አባቶች የልጆቻቸውን ራስ እየደባበሱም ልጆች ሆይ :- “Demonstrate, do not explicate” ይሏቸዋል፡፡ እንዲህ ያለውን የይሁዲዎችን ብልጠት የሚያውቁ ሸርዳጅ ፖለቲከኞች፤ ይሁዲዎች ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸው ዘመን የጠገበ ቁርሶ ያልተፈታው እነ ዳዊት፣ እነ ሳምንሶንና የመሳሰሉት የቀደሙ አባቶቻችን እንዳደረጉት የጠላቶቻችንን የወገብ አጥንትና የእግሮቻቸውን ቅልጥም እየሰበርን ሰጥ ለጥ እናደርጋቸዋለን የሚሉ ፖለቲከኞች በዳዊት መንበር ላይ በመቀመጣቸው ነው እያሉ በሽርደዳ ልባቸው በስቅታ እስኪፋቅ ድረስ ያብጠለጥሏቸዋል፡፡ ይህቺን የይሁዲዎች አሪፍ ብልሀት የትኛዋ አማልዕክት በየትኛዋ ሴት ተመስላ እንዳስጠናችው አናውቅም እንጂ ከአመታት በፊት አሜሪካዊው ቢል ክሊንተን ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደር ተጠቅሞባት ነበር፡፡ የአሜሪካኖች መላ ነገራቸው የተሠራው ከዶላር ደምና አጥንት መሆኑንና በወቅቱ የነበረው የአሜሪካ ኢኮሚኖሚ ለውድቀት እያኮበኮበ እንደሆነ በጊዜ ነቄ ያለው ክሊንተን፤ በምረጡኝ ዘመቻው አሜሪካኖቹን በደንብ አድርጐ የነገራቸው ሁለት ነገሮችን ነበር፡፡ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በመላሸቁ የነሳ የእያንዳንዳችን ገቢ ተራቁቶ ቦርሳችን ውስጥ የምናገኘው አንድ ኮካኮላ እንኳ መግዛት የማይችል ሽርፍራፊ ሳንቲሞች ብቻ ናቸው፡፡ እኔን፣ ብትመርጡኝ አመት ሁለት አመት መጠበቅ ሳያስፈልጋችሁ፣ በአንድ መቶ ቀናት ውስጥ ብቻ በዚህ “ስቹፒድ” በሆነው ኢኮኖሚ የተነሳ የተራቆተውን ቦርሳችሁን በዶላር እሞላላችኋለሁ አላቸው፡፡ አፉን ከፍቶ ሲያዳምጥ የነበረ ምድረ አሜሪካኔ ሁሉ የቦርሳውን ነገር ሲያስተውል በእርግጥምተራቁቷል፡፡ ታዲያ በአንድ መቶ ቀናት ብቻ የተራቆተውን ቦርሳችንን በዶላር የሚሞላልን ከሆነ ለጆርጅ ቡሽ (ያኔ አባትየው ቡሽ ነበር ለድጋሚ ምርጫ ከክሊንተን ጋር ይፎካከር የነበረው) ተጨማሪ አራት አመት ምን በወጣን ብለን እንጨምርለታለን እያለ ድምፁን ለቢል ክሊንተን ሠጠና ፕሬዚዳንት አድርጐ መረጠው፡፡ ተመራጩ ፕሬዘዳንት ቢል ክሊንተንም ልክ እንደ ይሁዲ ልጆች የተማረውን በሚገባ ያስታውስ ነበረና፣ ልክ እንዳለው ሁሉ ስልጣን በያዘ በአራተኛው ወር ኢኮኖሚው እንዲያገግምና የተራቆተው ቦርሳቸው በዶላር እንዲሞላ ማድረግ ቻለ፡፡ ክሊንተን በተግባር ሠርቶ ያሳያቸውን በደንብ የተገነዘቡት አሜሪካኖች፤ ከአራት አመት በኋላም በድጋሚ በመምረጥ ተጨማሪ አራት የስልጣን አመታትን አሻሩት፡፡ ልክ ናቸዋ!በተሠማሩበት የስራ መስክና በተሾሙበት የሃላፊነት ቦታ እንኳን ያልሠሩትን የሠሩትንም ሥራ ቢሆን በክርክርና ከፍ ባለ ሙግት ሊያሳምኑን ከሚንደቀደቁት ይልቅ ያለአንዳች አንጀባና ልፍለፋ ያከናወኑትን ስራ በተግባር እነሆኝ የሚሉ በእርግጥም ብፁአን ናቸው፡፡ ጓድ ሌኒን ለቦልሸቪክ ፓርቲ በአንድ ወቅት እንደተናገረው (መቸም ተናግሮት ሊሆን ይችላል ብለን ስላሰብን) ተግባር እንጂ ቃል መቸም ቢሆን ገለልተኛ አቋም ወስዶ አያውቅም፡፡ እናም አንድ ሰው ያልሠራውንም እንኳ ቢሆን ሰርቸዋለሁ ብሎ ካመነ፣ ቃላት ያንን ስራ እንዳልሠራው የማሳመን ችሎታቸውና እድላቸው የዜሮ ያህል ነው፡፡ አፋጠው የያዙት ጊዜም ሳያውቀው የመቀበሪያ ጉድጓዱን በገዛ እጁ እስኪቆፍር ድረስ ይበልጥ በሙግቱና በክርክሩ ይገፋበታል፡፡ ከእኔ ወዲያ ሠራተኛ፣ ከእኔ ወዲያ የልማት አርበኛ ላሳር የሚልና ሌሎቹን አጥብቆ የሚንቅ ከሆነማ እንኳን ተራው ሰው ሶቅራጥስ ራሱ የተኛበትን መቃብር ፈንቅሎ ቢመጣ ሁኔታውን ሊቀይረው አይችልም፡፡ በክርክርና በሙግት ብቻ ስራቸውን ለማሳመንና ድል ለማድረግ የሚጣጣሩ ሰዎች በሚቀጥለው ቀን ከአማልእክቶች የሚበረከትላቸው ስጦታ፤ ከሰዎች መገለል በሰዎች መጠላትና የመቃብር ሳጥናቸው ነው፡፡ ይህንን ታሪክ ስንነግራችሁ እያሟረትን እንዳይመስላችሁ፤ በክርክርና በሙግት ብቻ ስራቸውን ለማሳመን ከሚጣጣሩት ቀሽሞች ይልቅ የሠሩትን ወይም የሚሠሩትን ነገር በተግባር የሚያሳዩት የልባቸውን መሻትና ከሁሉም የላቀውን ድል እንደሚጨብጡ “ወይዘሮ የአለም ታሪክ” በርካታ ተጨባጭ አብነቶችን እየጠቀሰች፣ ቄንጠኛ ትረካዋን ስታስኮመኩመን ኖራለች እኮ! እኛም ያለውን የወረወረ ምን አይባልም እንደሚባለው ሁሉ፤ “ከወይዘሮ የአለም ታሪክ”ሰማነውንና ደባሪው የኑሮቀንበር ሸክሙ በከበደን ጊዜ በጥበባቸው ህይወታችንን የሚያለዝቡልን ጠበብት፣ አንብበን እንደሰት ዘንድ ጽፈው ካስቀመጡልን እየቀነስን እነሆ በረከት እንላችኋለን፡፡ ታሪክ አንድ የእመብርሃን ልጅ እየሱስ ከመወለዱ በፊት በ131 አመተ አለም የሮማ ገዥ የነበረው ፑብሊየስ ክራስስ ዲቨስ ሙሲያነስ፤ በወታደሮቹ ከብቦ የያዛትን ፐርጋመስ የተሰኘችውን የግሪክ ከተማ ዋናውን ቅጥሯን ሰብሮ ለመግባት የሚያስችለው ከፍተኛ ጥንካሬ ክብደትና ርዝመት ያለው ብረት አስፈለገው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በአቴንስ የመርከቦች መነሀሪያ ውስጥ ቆመው ከነበሩት መርከቦች ውስጥ አንድ ሁለት በሚሆኑት መርከቦች ላይ ተገጥሞ ያየው ትላልቅ የብረት የመርከብ ቀንድ ትዝ አለውና ከሁሉም ትልቅ የሆነውን መርጠው ባስቸኳይ እንዲያመጡለት ወታደሮቹን ላካቸው፡፡ የአገረ ገዥውን አስቸኳይ መልእክት የተቀበለው የመርከብ ኢንጂነር ግን አገረ ገዢው ለሚፈልገው ጉዳይ ከረጅሙ ይልቅ አጭሩየ መርከብ ብረት እንደሆነ እርግጠኛ በመሆን ወታደሮቹ ይዘው እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡ ወታደሮቹም እንዲያመጡ የታዘዙት ረጅሙን የመርከብ ብረት እንጂ አጭሩን እንዳልሆነ ቢነግሩትም ኢንጂነር ሆዬ፣ ለአረ ገዥው የሚጠቅመው አጭሩ የመርከብ ብረት እንጂ ረጅሙ እንዳልሆነ አጥብቆ እየተከራከረ በጅ አልል አለ፡፡ የታዘዙት ወታደሮች አገረ ገዢው የሚከራከሩት ሰው እንዳልሆነ በመጥቀስ፣ ኢንጂነሩ የታዘዘውን ረጅሙን ብረት እንዲልክለት አጥብቀው ቢማፀኑትም፣ የአጭሩን ብረት ጠቀሜታ የበለጠ ለማስረዳት በርካታ ንድፎችን በመንደፍ ከወዲያ ወዲህ እየተሽከረከረ መከራከሩንና ወታደሮቹን ለማሳመን መጣሩን ቀጠለ፡፡ የኢንጂነሩ ንድፍና ክርክር ምንም ስሜት ያልሰጣቸውና የአገረ ገዢውን ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ወታደሮች ኢንጂነሩ ስለ ጉዳዩ ያለውን እውቀትና እየሰጣቸው ያለውን ገለፃ ለጊዜው አቁሞ የአገረ ገዢውን ትዕዛዝ እንዲቀበል የመጨረሻ ልመናቸውን አቀረቡለት፡፡ ኢንጂነሩ

 

ግን ኢንጂነር ነበር፡፡ በመጨረሻ ስለ አጭሩ የመርከብ ብረት ጥቅም ይህን ያህል አስረድቻቸው ሊገባቸው ያልቻለው እንዴት ያሉ ደደቦች ቢሆኑ ነው እያለ የተገረመው ኢንጂነር፤ የታዘዘውን ሳይሆን በራሱ ፍላጐት አጭሩን የመርከብ ብረት ለአገረ ገዢው እንዲሠጡት አስይዞ ላካቸው፡፡ ወታደሮቹ እንደሄዱ “ደደብ ሰዎችን ማስረዳት እንዴት ያለ አበሳ ነው ለካ! የሮማ ጦር ሠራዊት እንደነዚህ ያሉ ድንጋይ ራሶችን በአባልነት መቀበሉ በእውነት እጅግ የሚያሳፍር ነገር ነው፡፡ አገረ ገዢው የላኩለት አጭር የመርከብ ብረት እሱ ለሚፈልገው ጉዳይ እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ሲረዳና በኢንጂነርነት ጥበቤ ተደንቆ ሽልማት ሲሸልመኝ ምናልባት ትንሽ ሊገባቸው ይችል ይሆናል” እያለ በኢንጂነርኛ ተሳለቀባቸው፡፡ወታደሮቹ አጭሩን የመርከብ ብረት ለአገረ ገዢው ሲያቀርቡለት እርሱ እንዲያመጡላት ያዘዛቸውን ረጅሙን የመርከብ ብረት ለምን እንዳላመጡት ጠየቃቸው፡፡ ወታደሮቹ የኢንጂነሩን ማለቂያ የሌለው ገለፃና ሙግት አስረዱት፡፡ አገረ ገዢ ሙሲያነስ በንዴት ጦፈ፡፡ የሮማን ባለስልጣን ትዕዛዝ አልቀበልም ማለት ታላቁን የሮማ ንጉሠ ነገስት መንግስት መናቅ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት ታላቅ ወንጀል የሠራ ደግሞ ዋጋው ምሱ ሞት ነው፡፡ አገረ ገዥ ሙሲያነስ ከንዴቱ የተነሳ በፐርጋመስ ከተማ ላይ ሊወስደው ስላሰበው ወታደራዊ እርምጃ ማሰብና ማተኮር አቃተው፡፡ በመጨረሻ ግን አንድ ውሳኔ ወሰነ፡፡ የእሱንና የሮማን ክብር ያዋረደውን ኢንጂነር ይዘው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡ ኢንጂነሩ ከፊቱ እንደቀረበ፣ ትዕዛዙን ለምን እንዳልተቀበለ ጠየቀው፡፡ በመርከብ ኢንጂሪንግ እውቀቱ ከልክ በላይ የተኮፈሰው ኢንጂነር፤ ስህተቱን አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ አገረገዢው ህይወቱን እንዲያተርፍለት እንዲለምነው ወታደሮቹ የሠጡትን ምክር መቀበል አልፈለገም፡፡ ልክ ለወታደሮቹ እንዳደረገው ሁሉ ከወዲያ ወዲህ እየተንጐራደደ፤ አገረ ገዢው የተሳሳተ ትዕዛዝ እንደሰጠ፣ ይህንንም ያደረገው የኢንጂነሪንግ እውቀት ስለሌለው እንደሆነ በመጥቀስ ከረጅሙ ይልቅ አጭሩ የመርከብ ብረት እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ለሰአታት ያለማቋረጥ አስረዳ፡፡ በመጨረሻም ምንጊዜም እንደሱ ያሉ አዋቂዎችን ምክር ቢሰማ የተሻለ እንደሚሆን አገረ ገዢውን መከረው፡፡ አገረ ገዢ ሙሲያነስ መላ ሰውነቱን የሚያቃጥለውን ንዴት እንደምንም ተቆጣጥሮ፣ ኢንጂነሩ አስረድቶ እስኪጨርስ ድረስ ጠበቀው፡፡ ከዚያም ወታደሮቹ የለበሰውን ልብስ አስወልቀው እጅና እግሩን እንዲያስሩት ካስደረገ በሁዋላ በጅራፍና በዱላ እስኪሞት ድረስ አስደበደበው፡፡ እንግዲህ ልብ አድርጉ! ታሪክ የአገረ ገዢውን የሙስያስን እንጂ የኢንጂነሩን ስም አልመዘገበውም፡፡ ነገር ግን ኢንጂነሩ እድሜውን መርከብ ሲነድፍ የኖረና ባለው የመርከብ ኢንጂነሪንግ እውቀቱ ከተማይቱም አለኝ ብላ የምትኮራበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለወታደሮቹም ሆነ ለአገረ ገዢው ያስረዳቸው ነገርምትክክለኛና በተግባር ተፈትኖ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢንጂነሩ የጥበቡንና የእውቀቱን ልክ በከፍተኛ ማስተዋል በስራ ሳይሆን በተራ ገለፃና ሙግት ማስረዳትና ማሳመን የሚወድ፣ በመካከላችን ከሚገኙት ዓይነት ሙግት አፍቃሪ ሠዎች እንደ አንዱ ነበር፡፡ ኢንጂነሩ የአገረ ገዢውን ትዕዛዝ ለምን እንዳልተቀበለ ለማስረዳት ለረጅም ሰአት የተሟገተውና የተከራከረው፣ አገረ ገዥ ሙሲያነስ ሳይንስ ገለልተኛ፣ ምክንያት ደግሞ ከሁሉም የላቀ ጉዳይ እንደሆነ ማስረዳት እችላለሁ በሚል ነበር፡፡ ነገር ግን እንደ ሌሎች ተከራካሪና ተሟጋች ሠዎች ሁሉ ይህ ኢንጂነርም የዘነጋው አንድ ትልቅ ጉዳይ፣ ቃላቶች እንደ ሳይንስ ገለልተኛ እንዳልሆኑና በስልጣን ከእኛ ከሚበልጥ ሠው ጋር አምርረን ስንከራከር ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የባለስልጣኑን የመረዳት ብቃት አሳንሶ እንደማየት ተደርጐ እንደሚቆጠርብን ነው፡፡ እያንዳንዱ ሠው ለራሱ ትክክል ነኝ ብሎ እንደሚያምነውና ቃላቶችም እውነቱ የዚህ ተቃራኒ እንደሆነ የሚያሳምኑት ዘንቦ ተባርቆ በመሆኑ የተሟጋችና የተከራካሪው ምክንያታዊነት ሰሚ ጆሮ የሚያገኙት ከስንት አንዴ በስለት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ተከራካሪ ሠዎች ወደ ጥጉ በተገፉ ቁጥር ይበልጥ እየተሟገቱና እየተከራከሩ ይሄዳሉ፡፡ በዚህም የራሳቸውን መቃብር በራሳቸው ይቆፍራሉ፡፡ ያላቸውን እውቀት ወይም የሠሩትን ስራ ለማሳመን ከድርጊት ይልቅ ሙግትና ክርክርን ስለሚመርጡ በሚሟገቱበት አሊያም በሚከራከሩበት ጊዜም የሚሟገቱትን ሠው የመረዳትም ሆነ  የአዕምሮ ብቃት ዝቅ አድርገው በመገመት ስለሚንቁት፣ እንኳን ተራ ሰው በአንደበተ ርቱእነቱና በላቀ የማሳመን ችሎታው አለም መጀን ያለችበት ሶቅራጥስ ራሱ ከሞት ተነስቶ ቢመጣም እንኳ ሁኔታውን አይቀይረውም፡፡ የመርከብ ኢንጂነሩም የገጠመው  ይሄው ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ሁኔታ ራሳቸውን በሚጐዳ መልኩ ሳይሆን ይልቁንም ትልቅ ጥቅም በሚያስገኝ ሁኔታ በመጠቀም ማሳለፍ የሚችሉ፣ ስራቸውንም ሆነ እውቀታቸውን በሙግትና በባዶ ክርክር ሳይሆን በላቀ ስራ ማሳየት የሚችሉ እንደ ጣሊያናዊው የስነ ጥበብ አድባር ማይክል አንጀሎ ያሉት ጥበበኛና ልባም ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡

ታሪክ ሁለት

በ1502 ዓ.ም እንዲህ ሆነ፡፡ በጣሊያኗ የፍሎረንስ ከተማ በሚገኘው የሳንታ ማርያ ዴል ፊዮሪ ቤተክርስቲያን የስራ ቤት ውስጥ አንድ ትልቅ የእምነበረድ ጥርብ ተቀምጦ ነበር፡፡ ይህ ትልቅ የእምነበረድ ድንጋይ የተቀመጠው አንድ ታላቅ ቅርጽ ሊበጅለት ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ቀሽም ቀራጭ የቅርጹ እግር የሚያርፍበትን ቦታ በስህተት ቦርቡሮ በሳውና ያን የመሠለ የእምነበረድ ጥርብ መና አስቀረው፡፡ በዚህ ቀሽም ቀራጭ አጓጉል ድርጊት የበሸቁት የአውሮፓ የስነ ጥበብ ከተማ እየተባለች በቁልምጫ የምትጠራው የፍሎረንስ ከተማ ከንቲባ ፒየሮ ሶደሪኒ፤ የእምነበረድ ጥርቡ ከመጣል የሚተርፍበትን ዘዴ ሲያሠላስሉ ከቆዩ በሁዋላ ይህንን ማድረግ የሚችለው  ዝነኛው ሠአሊ ሊዎናርዶ ዳቪንቺ ብቻ እንደሆነ በማመን አንድ ነገር እንዲያደርገው ኮንትራት ሊሠጡት ቢፈልጉም እምነበረዱ ተቦርቡሮ የተበሳበት ሁኔታ ተስፋ አስቆርጧቸው ነገር አለሙን ሁሉ ጨርሰው ተውት፡፡ በሳንታ ማርያ ዴል ፊዮሪ ቤተክርስቲያን ለመሳለም በሄዱ ቁጥር ያን የእምነበረድ ጥርብ ከስራ ቤቱ ጥግ ላይ አቧራ ለብሶ ሲያዩት ግን ቁጭታቸው  ይነሳል፡፡ ከእለታት ባንዱ ቀን ግን የስነጥበብ አማልዕክቶች ያነሳሱት የታላቁ ቀራጭ የማይክል አንጀሎ ጓደኞች፣ ያን የእምነበረድ ድንጋይ የሆነ የጥበብ ስራ በመስራት ማትረፍ የሚችለው እርሱ እንደሆነ በመተማመን፣ በወቅቱ በሮም ከተማ ይኖር ለነበረው ጓደኛቸው ደብዳቤ ፃፉለት፡፡ ታላቅ የስነ ጥበብ ዛር በአናቱ ላይ የሠፈረበት ማይክል አንጀሎም ዛሬ ነገ  ሳይል እለቱኑ ሲገሰግስ ፍሎረንስ ከተማ ደረሰና በቤተክርስቲያኑ በመገኘት የእምነበረዱን ድንጋይ ሁኔታ ከተመለከተ በሁዋላ፣ ድንጋዩ ተቦርቡሮ ከተበሳበት ሁኔታ ጋር የሚስማማ አንድ አሪፍ ቅርጽ መቅረጽ እንደሚችል ለጓደኞቹና በተለይ ደግሞ ድንጋዩን ባዩት ቁጥር ለሚቆጩት ለከተማዋ ከንቲባ ተናገረ፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒ ግን ጊዜውን በከንቱ እንዳያባክን በመምከር አጥብቀው ተከራከሩት፡፡ በመጨረሻ ግን በጓደኞቹ ግፊትና ማግባባት ስራውን እንዲሠራ ኮንትራቱን ሠጡት፡፡ ማይክል አንጀሎም ያን ግዙፍ የእምነበረድ ጥርብ ድንጋይ እንደገና አጠናና፣ ትንሹ ዳዊት ጐልያድን ለመግጠም ወንጭፉን ሲያስወነጭፍ የሚያሳይ ምስል ለመቅረጽ ወስኖ ስራውን ጀመረ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ስራውን አጠናቆ የመጨረሻ ጥራቢ አሸዋውን እያራገፈ እያለ፣ ድንገት ከንቲባ ሶዶሪኒ ከች አሉበት፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒ በፍሎረንስ ከተማ ተወልደው በማደጋቸው የተነሳ፣ በስነ ጥበብ ጉዳይ “ከኛ ወዲያ ሳሚ ንፍጥ ለቅላቂ” ባይ ነበሩና ቅርፁን እየተዘዋወሩ በማየት መገምገም ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ማይክል አንጀሎን እንዲህ አሉት:- “የቀረጽከው ቅርጽ በእውነቱ አስደሳች ነው፤ ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ ትንሽ ስህተት የሠራህ ይመስለኛል፡፡ አየህ ማይክል፤ የቅርጹ

አፍንጫ በጣም ተልቋል፡፡ ስለዚህ መላ ውበቱን አጥፍቶታል፡፡”ከንቲባ ሶደሪኒ ይህን አስተያየት ሲሠጡ በጥሞናና በፀጥታ ያዳመጣቸው ማይክል አንጀሎ፤ ለከንቲባው አስተያየት መነሻ የሆነው ዋና ጉዳይ ማለትም የቅርፁ አፍንጫ በጣም ረዝሞ የታያቸው ቅርጹን ማየት በሚገባቸው ቦታ ላይ ሳይሆን ከታች ወደ ላይ ስላዩት እንደሆነ የገባው ወዲያውኑ ነበር፡፡ እናም ማይክል አንጀሎ የሠራው ቅርጽ ትክክለኛ እንደሆነ ለማስረዳት አንዳች ቃል ሳይተነፍስ፣ ከመራገፍ የተረፈ ጥራቢ አሸዋና የመቅረጫ መሮውን በመያዝ ከንቲባ ሶደሪኒ በመቅረጫ

መሰላሉ ላይ እንዲወጡ ጋበዛቸው፡፡ ከንቲባው እንደተባሉት በመሰላሉ ላይ በመውጣት ትክክለኛው የእይታ ቦታ ላይ መቆማቸውን ሲያረጋግጥ፣ የቅርፁን አፍንጫ በያዘው መሮ በቀስታ ነካ ነካ በማድረግና የያዘውን ጥራቢ አሸዋ በማፍሰስ፣ የቅርፁን አፍንጫ ጨርሶ ሳይነካ የባለስልጣኑን ትዕዛዝ ተቀብሎ የማስተካከያ ስራ እንደሠራ አስመስሎ በትህትና እንዲህ አላቸው፡- “ጌታዬ እስኪ አሁን ይመልከቱት! እንዴት ነው?”  ማግኒፊሸንት! ብራቮ … ብራቮ፡፡ በአንዴ እንደገና ፈጠርከው እኮ … ነፍስ እኮ ነው የዘራህበት! ብራቮ … ብራቮ!” ከንቲባ ሶደሪኒ በደስታፈነጠዙ፡፡ እንግዲህ ልብ አድርጉ፡፡ ምንም እንኳ እሱ በኖረበት ዘመን ኖረን በአካል ባናውቀውም፣ ለድፍን አለሙ ሁሉ ትንግርት የሆኑ ስራዎቹን ትቶ ያለፈው ማይክል አንጀሎ በቃ ማይክል አንጀሎ ነው፡፡ ስለዚህ ከንቲባ ሶደሪኒ እንደፈለጉት የቅርፁን አፍንጫ ቢያሳጥረው ኖሮ የዚያ ቅርጽና የእምነበረድ ጥርብ ድንጋይ ነገር አለቀ ደቀቀ ነበር፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒን ተሳስተዋል ብሎ በድርቅና ቢከራከራቸውና የልባቸውን መሻት ባይሞላላቸው ኖሮ ደግሞ እሳቸውን ከማስቀየምና ወደፊት ሊሠጡት የሚችሉትን የስራ ኮንትራት ከማስቀረት በቀር የሚያገኘው አንዳችም አይነት ጥቅም አልነበረም፡፡ ማይክል አንጀሎ ግን ነቄ ጥበበኛ ነበረና ዛሬም ድረስ ልክ እንደ አዲስ የጥበብ ስራ መላው አለም የሚያደንቀውን የዳዊትን ቅርጽ ሳይነካ የከንቲባ ሶደሪኒን ፍላጐትም በአጓጉል ክርክር ሳይቃወም ያደረገውን አደረገ - “እንዴ! ቃላቶች በሌላው ሠው ስሜትና ስጋት መጠን፣ የመተርጐም እጅግ አስጠሊታና አደገኛ ችሎታ እንዳላቸው ያወቅሁት ገና ጥንት እኮ ነው” እያለ፡፡ መቼም ምንም ቢሆን ማይክል አንጀሎን መሆን አንችልም፡፡ ነገር ግን የእሱን ልባምነትና የነገሮችን ቀጣይ ውጤት ምንነት በሚገባ የመረዳት የአዕምሮ ንቁነትን መኮረጅ እንችላለን፡፡ ስራችንን ወይም እምነታችንን ለማስረዳት በምናደርገው የተሟሟቀ ክርክርና ሙግት ጉዳያችንን የሚደግፍ የሚመስለንን ነገር ሁሉ መናገር፣ መጽሀፍ ቅዱስን ወይም ቅዱስ ቁርአን መጥቀስ አሊያም ሊረጋገጥ የማይችል የስታትስቲክስ ቁጥር ሁሉ መጥቀስ እንችላለን፡፡ ቃል ግን ቃል ብቻ ነው፡፡ ስራና ተግባር ግን ከሁሉም የበለጠ ትርጉም የሚሠጥና ጠንካራ ነው፡፡ የሠሩትን ወይም የሚሠሩትን በወሬ ወይም በክርክር ሳይሆን በስራ ብቻ ማሳየት እንደ ንግግር ሰው አያስቀይምም፡፡ እንደየሠው ስሜትና ስጋት መጠን እንደተፈለገው አይተረጐምም፡፡ እርግጥ ነው ልጆች ሳለን የክርስትና ሃይማኖት መሪዎች “ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው” እያሉ ቢያስተምሩንም ስመጥሩው ባለቅኔና ፈላስፋ ባልታዛር ግራሽያን “እውነት ባጠቃላይ ይታያል እንጂ የሚሠማው ከስንት አንድ ነው” ያለውም ምንም አቃቂር የሚወጣለት አይደለም፡፡ በመጨረሻ እንዲህ እንላለን፡፡ እንደ ማይክል አንጀሎ የሠራውን ሥራ በዲስኩርና በሙግት ሳይሆን በተግባር የሚያሳይ አስተዋይ ልበ ብሩህ መሪ ያገኙ ህዝቦች ብፁአን ናቸው፡፡ አሜን!! ዲስኩርና ሙግት ሳይሆን ሥራ!በአለማችን ላይ ታትመው እናነባቸው ዘንድ እነሆ በረከት ከተባልነው ተቆጥረው የማያልቁ መጽሐፍት ውስጥ እድሜ ዘመናችንን ሁሉ ስናነበው ብንኖር ረቂቅነቱ የማይጓደልና ሁሌም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነበብነው ያህል ሆኖ ከሚሰማን ድንቅ መጽሐፍት አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው (ቅዱስ ቁርአንም እንዲሁ)በዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታዲያ ለበርካታ ጊዜያት ተደጋግሞ የተገለፀ አንድ አሪፍ ጉዳይ አለ፡፡ እግዜር ሽርካችን ስለሆነ እኛን ባይጠላንም ከሁላችንም አስበልጦ የሚወዳቸውና የመረጥኩት ህዝቤ እያለ የሚጠራቸው ይሁዲዎችን ነው፡፡ እግዜር እነሱን ከሁሉ አስበልጦ ቢወዳቸውና ቢመርጣቸውም እነሱ ግን አንድም ጊዜ የልቡን

አድርሰውለትና እርሱ እንደሚፈልገው ሽርኩና ታዛዥ ሆነውለት አያውቁም፡፡ ሙሴ ከግብጽ እየመራ ሲያወጣቸው የሠሩት ስራ ሰውየው ሙሴ ባይሆን ኖሮ፣ በዚያ በረሃ ጣጥሏቸው የትሜናው በሄደ ነበር፡፡ እግዜር በተራቡ ጊዜ ከሠማይ መናን አውርዶ ከመገባቸው በኋላ
ትንሽ ሲጠግቡ እግዜርን እንሸውደው ተባብለው ጣኦት ማምለካቸውን ጀምረው ነበር፡፡ ያኔ ታዲያ በዚህ የማይገባ ድርጊታቸው የተቆጣው እግዜር፤ ለምን ይሄን ድርጊት ፈፀማችሁ እያለ ከነሱ ጋር አንዳችም ክርክርና ሙግት ሳይገጥም የሚገባቸውን ቅጣት በተግባር እየቀጣ ያሳያቸው ነበር - ማረን አጥፍተናል እስኪሉ ድረስ፡፡ ይሁዲዎቹ ከዚያ ትምህርት ወስደው ነው መሠል በክርክርና በተግባር ማሳየትን በተመለከተ
በየአጋጣሚው ሁሉ የሚናገሯት አንድ አሪፍ አባባል አላቸው፡፡ ነገርየዋ እንዲህ የምትል ናት:- “በክርክርና በሙግት ተገኘ የሚባል ጊዜአዊ ድል አክሳሪ ድል ነው፡፡ ክርክሩና ሙግት ካስገኘው ድል ይልቅ የሚፈጥረው የቅሬታና የመከፋት ስሜት ከድሉ ስሜትና ከሌላ የሃሳብ ለውጥ የበለጠ ለረጅም ጊዜ በሰዎች ልብ ውስጥ ይኖራል፡፡”የይሁዲ አባቶች ልጆቻቸውን፤ “ሰዎች ከእናንተ ሃሳብ ጋር እንዲስማሙ ከፈለጋችሁ በክርክርና
በሙግት ለማሳመን ከመጣጣር ይልቅ ሠርቶ በተግባር ማሳየት የበለጠ የማሳመን ሃይል አለው፡፡” እያሉ አጥብቀው ይመክሯቸዋል፡፡ እነዚህ የይሁዲ አባቶች የልጆቻቸውን ራስ እየደባበሱም ልጆች ሆይ :- “Demonstrate, do not explicate” ይሏቸዋል፡፡
እንዲህ ያለውን የይሁዲዎችን ብልጠት የሚያውቁ ሸርዳጅ ፖለቲከኞች፤ ይሁዲዎች
ከፍልስጤማውያን ጋር ያላቸው ዘመን የጠገበ ቁርሶ ያልተፈታው እነ ዳዊት፣ እነ ሳምንሶንና የመሳሰሉት የቀደሙ አባቶቻችን እንዳደረጉት የጠላቶቻችንን የወገብ አጥንትና የእግሮቻቸውን ቅልጥም እየሰበርን ሰጥ ለጥ እናደርጋቸዋለን የሚሉ ፖለቲከኞች በዳዊት መንበር ላይ በመቀመጣቸው
ነው እያሉ በሽርደዳ ልባቸው በስቅታ እስኪፋቅ ድረስ ያብጠለጥሏቸዋል፡፡ ይህቺን የይሁዲዎች አሪፍ ብልሀት የትኛዋ አማልዕክት በየትኛዋ ሴት ተመስላ እንዳስጠናችው አናውቅም እንጂ ከአመታት በፊት አሜሪካዊው ቢል ክሊንተን ለመጀመሪያ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት
ሲወዳደር ተጠቅሞባት ነበር፡፡ የአሜሪካኖች መላ ነገራቸው የተሠራው ከዶላር ደምና አጥንት መሆኑንና በወቅቱ የነበረው የአሜሪካ ኢኮሚኖሚ ለውድቀት እያኮበኮበ እንደሆነ በጊዜ ነቄ ያለው ክሊንተን፤ በምረጡኝ ዘመቻው አሜሪካኖቹን በደንብ አድርጐ የነገራቸው ሁለት ነገሮችን ነበር፡፡
የአሜሪካ ኢኮኖሚ በመላሸቁ የነሳ የእያንዳንዳችን ገቢ ተራቁቶ ቦርሳችን ውስጥ የምናገኘው አንድ ኮካኮላ እንኳ መግዛት የማይችል ሽርፍራፊ ሳንቲሞች ብቻ ናቸው፡፡ እኔን፣ ብትመርጡኝ አመት ሁለት አመት መጠበቅ ሳያስፈልጋችሁ፣ በአንድ መቶ ቀናት ውስጥ ብቻ በዚህ “ስቹፒድ” በሆነው ኢኮኖሚ የተነሳ የተራቆተውን ቦርሳችሁን በዶላር እሞላላችኋለሁ አላቸው፡፡ አፉን ከፍቶ ሲያዳምጥ የነበረ ምድረ አሜሪካኔ ሁሉ የቦርሳውን ነገር ሲያስተውል በእርግጥም ተራቁቷል፡፡ ታዲያ በአንድ መቶ ቀናት ብቻ የተራቆተውን ቦርሳችንን በዶላር የሚሞላልን ከሆነ
ለጆርጅ ቡሽ (ያኔ አባትየው ቡሽ ነበር ለድጋሚ ምርጫ ከክሊንተን ጋር ይፎካከር የነበረው) ተጨማሪ አራት አመት ምን በወጣን ብለን እንጨምርለታለን እያለ ድምፁን ለቢል ክሊንተን ሠጠና ፕሬዚዳንት አድርጐ መረጠው፡፡ ተመራጩ ፕሬዘዳንት ቢል ክሊንተንም ልክ እንደ ይሁዲ ልጆች የተማረውን በሚገባ ያስታውስ ነበረና፣ ልክ እንዳለው ሁሉ ስልጣን በያዘ በአራተኛው ወር ኢኮኖሚው እንዲያገግምና የተራቆተው ቦርሳቸው በዶላር እንዲሞላ ማድረግ ቻለ፡፡ ክሊንተን በተግባር ሠርቶ ያሳያቸውን በደንብ የተገነዘቡት አሜሪካኖች፤ ከአራት አመት በኋላም በድጋሚ በመምረጥ ተጨማሪ አራት የስልጣን አመታትን አሻሩት፡፡ ልክ ናቸዋ!በተሠማሩበት የስራ መስክና በተሾሙበት የሃላፊነት ቦታ እንኳን ያልሠሩትን የሠሩትንም ሥራ ቢሆን በክርክርና ከፍ ባለ ሙግት ሊያሳምኑን ከሚንደቀደቁት ይልቅ ያለአንዳች አንጀባና ልፍለፋ ያከናወኑትን ስራ በተግባር እነሆኝ የሚሉ በእርግጥም ብፁአን ናቸው፡፡ ጓድ ሌኒን ለቦልሸቪክ ፓርቲ በአንድ ወቅት እንደተናገረው (መቸም ተናግሮት ሊሆን ይችላል ብለን ስላሰብን) ተግባር እንጂ ቃል መቸም ቢሆን ገለልተኛ አቋም ወስዶ አያውቅም፡፡ እናም አንድ ሰው ያልሠራውንም እንኳ ቢሆን
ሰርቸዋለሁ ብሎ ካመነ፣ ቃላት ያንን ስራ እንዳልሠራው የማሳመን ችሎታቸውና እድላቸው የዜሮ ያህል ነው፡፡ አፋጠው የያዙት ጊዜም ሳያውቀው የመቀበሪያ ጉድጓዱን በገዛ እጁ እስኪቆፍር ድረስ ይበልጥ በሙግቱና በክርክሩ ይገፋበታል፡፡ ከእኔ ወዲያ ሠራተኛ፣ ከእኔ ወዲያ የልማት አርበኛ ላሳር የሚልና ሌሎቹን አጥብቆ የሚንቅ ከሆነማ እንኳን ተራው ሰው ሶቅራጥስ ራሱ የተኛበትን መቃብር ፈንቅሎ ቢመጣ ሁኔታውን ሊቀይረው አይችልም፡፡ በክርክርና በሙግት ብቻ ስራቸውን ለማሳመንና ድል ለማድረግ የሚጣጣሩ ሰዎች በሚቀጥለው ቀን ከአማልእክቶች የሚበረከትላቸው ስጦታ፤ ከሰዎች መገለል በሰዎች መጠላትና የመቃብር ሳጥናቸው ነው፡፡ ይህንን ታሪክ ስንነግራችሁ እያሟረትን እንዳይመስላችሁ፤ በክርክርና በሙግት ብቻ ስራቸውን ለማሳመን ከሚጣጣሩት ቀሽሞች ይልቅ የሠሩትን ወይም የሚሠሩትን ነገር በተግባር የሚያሳዩት የልባቸውን መሻትና ከሁሉም የላቀውን ድል እንደሚጨብጡ “ወይዘሮ የአለም ታሪክ” በርካታ ተጨባጭ አብነቶችን እየጠቀሰች፣ ቄንጠኛ ትረካዋን ስታስኮመኩመን ኖራለች እኮ! እኛም ያለውን የወረወረ ምን አይባልም እንደሚባለው ሁሉ፤ “ከወይዘሮ የአለም ታሪክ” የሰማነውንና ደባሪው የኑሮ ቀንበር ሸክሙ በከበደን ጊዜ በጥበባቸው ህይወታችንን የሚያለዝቡልን ጠበብት፣ አንብበን እንደሰት ዘንድ ጽፈው ካስቀመጡልን እየቀነስን እነሆ በረከት እንላችኋለን፡፡ ታሪክ አንድ የእመብርሃን ልጅ እየሱስ ከመወለዱ በፊት በ131 አመተ አለም የሮማ ገዥ የነበረው ፑብሊየስ ክራስስ ዲቨስ ሙሲያነስ፤ በወታደሮቹ ከብቦ የያዛትን ፐርጋመስ የተሰኘችውን የግሪክ ከተማ ዋናውን ቅጥሯን ሰብሮ ለመግባት የሚያስችለው ከፍተኛ ጥንካሬ ክብደትና ርዝመት ያለው ብረት አስፈለገው፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊት በአቴንስ የመርከቦች መነሀሪያ ውስጥ ቆመው ከነበሩት መርከቦች ውስጥ አንድ ሁለት በሚሆኑት መርከቦች ላይ ተገጥሞ ያየው ትላልቅ የብረት የመርከብ ቀንድ ትዝ አለውና
ከሁሉም ትልቅ የሆነውን መርጠው ባስቸኳይ እንዲያመጡለት ወታደሮቹን ላካቸው፡፡ የአገረ ገዥውን አስቸኳይ መልእክት የተቀበለው የመርከብ ኢንጂነር ግን አገረ ገዢው ለሚፈልገው ጉዳይ ከረጅሙ ይልቅ አጭሩየ መርከብ ብረት እንደሆነ እርግጠኛ በመሆን ወታደሮቹ ይዘው እንዲሄዱ ነገራቸው፡፡
ወታደሮቹም እንዲያመጡ የታዘዙት ረጅሙን የመርከብ ብረት እንጂ አጭሩን እንዳልሆነ ቢነግሩትም ኢንጂነር ሆዬ፣ ለአረ ገዥው የሚጠቅመው አጭሩ የመርከብ ብረት እንጂ ረጅሙ እንዳልሆነ አጥብቆ እየተከራከረ በጅ አልል አለ፡፡ የታዘዙት ወታደሮች አገረ ገዢው የሚከራከሩት ሰው እንዳልሆነ በመጥቀስ፣ ኢንጂነሩ የታዘዘውን ረጅሙን ብረት እንዲልክለት አጥብቀው ቢማፀኑትም፣ የአጭሩን ብረት ጠቀሜታ የበለጠ ለማስረዳት
በርካታ ንድፎችን በመንደፍ ከወዲያ ወዲህ እየተሽከረከረ መከራከሩንና ወታደሮቹን ለማሳመን መጣሩን ቀጠለ፡፡ የኢንጂነሩ ንድፍና ክርክር ምንም ስሜት ያልሰጣቸውና የአገረ ገዢውን ማንነት ጠንቅቀው የሚያውቁት ወታደሮች ኢንጂነሩ ስለ ጉዳዩ ያለውን እውቀትና እየሰጣቸው ያለውን ገለፃ ለጊዜው አቁሞ የአገረ ገዢውን ትዕዛዝ እንዲቀበል የመጨረሻ ልመናቸውን አቀረቡለት፡፡ ኢንጂነሩ ግን ኢንጂነር ነበር፡፡
በመጨረሻ ስለ አጭሩ የመርከብ ብረት ጥቅም ይህን ያህል አስረድቻቸው ሊገባቸው ያልቻለው እንዴት ያሉ ደደቦች ቢሆኑ ነው እያለ የተገረመው ኢንጂነር፤ የታዘዘውን ሳይሆን በራሱ ፍላጐት አጭሩን የመርከብ ብረት ለአገረ ገዢው እንዲሠጡት አስይዞ ላካቸው፡፡
ወታደሮቹ እንደሄዱ “ደደብ ሰዎችን ማስረዳት እንዴት ያለ አበሳ ነው ለካ! የሮማ ጦር ሠራዊት እንደነዚህ ያሉ ድንጋይ ራሶችን በአባልነት መቀበሉ በእውነት እጅግ የሚያሳፍር ነገር ነው፡፡ አገረ ገዢው የላኩለት አጭር የመርከብ ብረት እሱ ለሚፈልገው ጉዳይ እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ሲረዳና በኢንጂነርነት ጥበቤ ተደንቆ ሽልማት ሲሸልመኝ ምናልባት ትንሽ ሊገባቸው ይችል ይሆናል” እያለ በኢንጂነርኛ ተሳለቀባቸው፡፡
ወታደሮቹ አጭሩን የመርከብ ብረት ለአገረ ገዢው ሲያቀርቡለት እርሱ እንዲያመጡላት ያዘዛቸውን ረጅሙን የመርከብ ብረት ለምን እንዳላመጡት ጠየቃቸው፡፡ ወታደሮቹ የኢንጂነሩን ማለቂያ የሌለው ገለፃና ሙግት አስረዱት፡፡ አገረ ገዢ ሙሲያነስ በንዴት ጦፈ፡፡ የሮማን ባለስልጣን ትዕዛዝ አልቀበልም ማለት ታላቁን የሮማ ንጉሠ ነገስት መንግስት መናቅ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለ ድፍረት የተሞላበት ታላቅ ወንጀል የሠራ ደግሞ ዋጋው ምሱ ሞት ነው፡፡ አገረ ገዥ ሙሲያነስ ከንዴቱ የተነሳ በፐርጋመስ ከተማ ላይ ሊወስደው ስላሰበው ወታደራዊ እርምጃ
ማሰብና ማተኮር አቃተው፡፡ በመጨረሻ ግን አንድ ውሳኔ ወሰነ፡፡ የእሱንና የሮማን ክብር ያዋረደውን ኢንጂነር ይዘው እንዲያመጡለት አዘዘ፡፡
ኢንጂነሩ ከፊቱ እንደቀረበ፣ ትዕዛዙን ለምን እንዳልተቀበለ ጠየቀው፡፡ በመርከብ ኢንጂሪንግ እውቀቱ ከልክ በላይ የተኮፈሰው ኢንጂነር፤ ስህተቱን አምኖ ይቅርታ በመጠየቅ አገረገዢው ህይወቱን እንዲያተርፍለት እንዲለምነው ወታደሮቹ የሠጡትን ምክር መቀበል አልፈለገም፡፡ ልክ ለወታደሮቹ እንዳደረገው ሁሉ ከወዲያ ወዲህ እየተንጐራደደ፤ አገረ ገዢው የተሳሳተ ትዕዛዝ እንደሰጠ፣ ይህንንም ያደረገው የኢንጂነሪንግ እውቀት ስለሌለው እንደሆነ በመጥቀስ ከረጅሙ ይልቅ አጭሩ የመርከብ ብረት እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ለሰአታት ያለማቋረጥ አስረዳ፡፡ በመጨረሻም ምንጊዜም እንደሱ ያሉአዋቂዎችን ምክር ቢሰማ የተሻለ እንደሚሆን አገረ ገዢውን መከረው፡፡ አገረ ገዢ ሙሲያነስ መላ ሰውነቱን የሚያቃጥለውን ንዴት እንደምንም ተቆጣጥሮ፣ ኢንጂነሩ አስረድቶ እስኪጨርስ ድረስ ጠበቀው፡፡ ከዚያም ወታደሮቹ የለበሰውን ልብስ አስወልቀው እጅና እግሩን እንዲያስሩት ካስደረገ በሁዋላ በጅራፍና በዱላ እስኪሞት ድረስ አስደበደበው፡፡ እንግዲህ ልብ አድርጉ! ታሪክ የአገረ ገዢውን የሙስያስን እንጂ የኢንጂነሩን ስም አልመዘገበውም፡፡ ነገር ግን ኢንጂነሩ እድሜውን መርከብ ሲነድፍ የኖረና ባለው የመርከብ ኢንጂነሪንግ እውቀቱ ከተማይቱም አለኝ ብላ የምትኮራበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለወታደሮቹም ሆነ ለአገረ ገዢው ያስረዳቸው ነገርም ትክክለኛና በተግባር ተፈትኖ የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ኢንጂነሩ የጥበቡንና የእውቀቱን ልክ በከፍተኛ ማስተዋል በስራ ሳይሆን በተራ ገለፃና ሙግት ማስረዳትና ማሳመን የሚወድ፣ በመካከላችን ከሚገኙት ዓይነት ሙግት አፍቃሪ ሠዎች እንደ አንዱ ነበር፡፡
ኢንጂነሩ የአገረ ገዢውን ትዕዛዝ ለምን እንዳልተቀበለ ለማስረዳት ለረጅም ሰአት የተሟገተውና የተከራከረው፣ አገረ ገዥ ሙሲያነስ ሳይንስ ገለልተኛ፣ ምክንያት ደግሞ ከሁሉም የላቀ ጉዳይ እንደሆነ ማስረዳት እችላለሁ በሚል ነበር፡፡ ገር ግን እንደ ሌሎች ተከራካሪና ተሟጋች ሠዎች ሁሉ ይህ ኢንጂነርም የዘነጋው አንድ ትልቅ ጉዳይ፣ ቃላቶች እንደ ሳይንስ ገለልተኛ እንዳልሆኑና በስልጣን ከእኛ ከሚበልጥ ሠው ጋር አምርረን
ስንከራከር ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የባለስልጣኑን የመረዳት ብቃት አሳንሶ እንደማየት ተደርጐ እንደሚቆጠርብን ነው፡፡ እያንዳንዱ ሠው ለራሱ ትክክል ነኝ ብሎ እንደሚያምነውና ቃላቶችም እውነቱ የዚህ ተቃራኒ እንደሆነ የሚያሳምኑት ዘንቦ ተባርቆ በመሆኑ የተሟጋችና የተከራካሪው ምክንያታዊነት ሰሚ ጆሮ የሚያገኙት ከስንት አንዴ በስለት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ተከራካሪ ሠዎች ወደ ጥጉ በተገፉ ቁጥር ይበልጥ እየተሟገቱና እየተከራከሩ ይሄዳሉ፡፡ በዚህም የራሳቸውን መቃብር በራሳቸው ይቆፍራሉ፡፡ ያላቸውን እውቀት ወይም የሠሩትን ስራ ለማሳመን ከድርጊት ይልቅ ሙግትና ክርክርን ስለሚመርጡ በሚሟገቱበት አሊያም በሚከራከሩበት ጊዜም የሚሟገቱትን ሠው የመረዳትም ሆነ  የአዕምሮ ብቃት ዝቅ አድርገው በመገመት ስለሚንቁት፣ እንኳን ተራ ሰው በአንደበተ ርቱእነቱና በላቀ የማሳመን ችሎታው አለም መጀን ያለችበት ሶቅራጥስ
ራሱ ከሞት ተነስቶ ቢመጣም እንኳ ሁኔታውን አይቀይረውም፡፡ የመርከብ ኢንጂነሩም የገጠመው  ይሄው ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ሁኔታ ራሳቸውን በሚጐዳ መልኩ ሳይሆን ይልቁንም ትልቅ ጥቅም በሚያስገኝ ሁኔታ በመጠቀም ማሳለፍ የሚችሉ፣ ስራቸውንም ሆነ እውቀታቸውን በሙግትና በባዶ ክርክር ሳይሆን በላቀ ስራ ማሳየት የሚችሉ እንደ ጣሊያናዊው የስነ ጥበብ አድባር ማይክል አንጀሎ ያሉት ጥበበኛና ልባም ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ታሪክ ሁለት በ1502 ዓ.ም እንዲህ ሆነ፡፡ በጣሊያኗ የፍሎረንስ ከተማ በሚገኘው የሳንታ ማርያ ዴል ፊዮሪ
ቤተክርስቲያን የስራ ቤት ውስጥ አንድ ትልቅ የእምነበረድ ጥርብ ተቀምጦ ነበር፡፡ ይህ ትልቅ የእምነበረድ ድንጋይ የተቀመጠው አንድ ታላቅ ቅርጽ ሊበጅለት ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ቀሽም ቀራጭ የቅርጹ እግር የሚያርፍበትን ቦታ በስህተት ቦርቡሮ በሳውና ያን የመሠለ የእምነበረድ ጥርብ መና አስቀረው፡፡ በዚህ ቀሽም ቀራጭ አጓጉል ድርጊት የበሸቁት የአውሮፓ የስነ ጥበብ ከተማ እየተባለች በቁልምጫ የምትጠራው የፍሎረንስ ከተማ ከንቲባ ፒየሮ ሶደሪኒ፤ የእምነበረድ ጥርቡ ከመጣል የሚተርፍበትን ዘዴ ሲያሠላስሉ ከቆዩ በሁዋላ ይህንን ማድረግ የሚችለው  ዝነኛው ሠአሊ ሊዎናርዶ ዳቪንቺ ብቻ እንደሆነ በማመን አንድ ነገር እንዲያደርገው ኮንትራት ሊሠጡት ቢፈልጉም እምነበረዱ ተቦርቡሮ የተበሳበት ሁኔታ ተስፋ አስቆርጧቸው ነገር አለሙን ሁሉ ጨርሰው ተውት፡፡ በሳንታማርያ ዴል ፊዮሪ ቤተክርስቲያን ለመሳለም በሄዱ ቁጥር ያን የእምነበረድ ጥርብ ከስራ ቤቱ ጥግ ላይ አቧራ ለብሶ ሲያዩት ግን ቁጭታቸው  ይነሳል፡፡ ከእለታት ባንዱ ቀን ግን የስነጥበብ አማልዕክቶች ያነሳሱት የታላቁ ቀራጭ የማይክል አንጀሎ ጓደኞች፣ ያን የእምነበረድ ድንጋይ የሆነ የጥበብ ስራ በመስራት ማትረፍ የሚችለው እርሱ እንደሆነ
በመተማመን፣ በወቅቱ በሮም ከተማ ይኖር ለነበረው ጓደኛቸው ደብዳቤ ፃፉለት፡፡ ታላቅ የስነ ጥበብ ዛር በአናቱ ላይ የሠፈረበት ማይክል አንጀሎም ዛሬ ነገ  ሳይል እለቱኑ ሲገሰግስ ፍሎረንስ ከተማ ደረሰና በቤተክርስቲያኑ በመገኘት የእምነበረዱን ድንጋይ ሁኔታ ከተመለከተ በሁዋላ፣ ድንጋዩ ተቦርቡሮ ከተበሳበት ሁኔታ ጋር የሚስማማ አንድ አሪፍ ቅርጽ መቅረጽ እንደሚችል ለጓደኞቹና በተለይ ደግሞ ድንጋዩን ባዩት ቁጥር ለሚቆጩት ለከተማዋ ከንቲባ ተናገረ፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒ ግን ጊዜውን በከንቱ እንዳያባክን በመምከር አጥብቀው ተከራከሩት፡፡ በመጨረሻ ግን በጓደኞቹ ግፊትና ማግባባት ስራውን እንዲሠራ ኮንትራቱን ሠጡት፡፡ ማይክል አንጀሎም ያን ግዙፍ የእምነበረድ ጥርብ ድንጋይ እንደገና አጠናና፣ ትንሹ ዳዊት ጐልያድን ለመግጠም ወንጭፉን ሲያስወነጭፍ የሚያሳይ ምስል ለመቅረጽ ወስኖ ስራውን ጀመረ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ስራውን አጠናቆ የመጨረሻ ጥራቢ አሸዋውን እያራገፈ እያለ፣ ድንገት ከንቲባ ሶዶሪኒ ከች አሉበት፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒ በፍሎረንስ ከተማ ተወልደው በማደጋቸው የተነሳ፣ በስነ ጥበብ ጉዳይ “ከኛ ወዲያ ሳሚ ንፍጥ ለቅላቂ” ባይ ነበሩና ቅርፁን እየተዘዋወሩ በማየት መገምገም ጀመሩ፡፡ በመጨረሻም ማይክል አንጀሎን እንዲህ አሉት:- “የቀረጽከው ቅርጽ በእውነቱ አስደሳች ነው፤ ነገር ግን አንድ ቦታ ላይ ትንሽ ስህተት የሠራህ ይመስለኛል፡፡ አየህ ማይክል፤ የቅርጹ አፍንጫ በጣም ተልቋል፡፡ ስለዚህ መላ ውበቱን አጥፍቶታል፡፡”
ከንቲባ ሶደሪኒ ይህን አስተያየት ሲሠጡ በጥሞናና በፀጥታ ያዳመጣቸው ማይክል አንጀሎ፤ ለከንቲባው አስተያየት መነሻ የሆነው ዋና ጉዳይ ማለትም የቅርፁ አፍንጫ በጣም ረዝሞ የታያቸው ቅርጹን ማየት በሚገባቸው ቦታ ላይ ሳይሆን ከታች ወደ ላይ ስላዩት እንደሆነ የገባው ወዲያውኑ ነበር፡፡ እናም ማይክል አንጀሎ የሠራው ቅርጽ ትክክለኛ እንደሆነ ለማስረዳት አንዳች ቃል ሳይተነፍስ፣ ከመራገፍ የተረፈ ጥራቢ አሸዋና የመቅረጫ መሮውን በመያዝ ከንቲባ ሶደሪኒ በመቅረጫ መሰላሉ ላይ እንዲወጡ ጋበዛቸው፡፡ ከንቲባው እንደተባሉት በመሰላሉ ላይ በመውጣት ትክክለኛው የእይታ ቦታ ላይ መቆማቸውን ሲያረጋግጥ፣ የቅርፁን አፍንጫ በያዘው መሮ በቀስታ ነካ ነካ በማድረግና የያዘውን ጥራቢ አሸዋ በማፍሰስ፣ የቅርፁን አፍንጫ ጨርሶ ሳይነካ የባለስልጣኑን ትዕዛዝ ተቀብሎ የማስተካከያ ስራ እንደሠራ አስመስሎ በትህትና እንዲህ አላቸው፡- “ጌታዬ እስኪ አሁን ይመልከቱት! እንዴት ነው?”  “ማግኒፊሸንት! ብራቮ … ብራቮ፡፡ በአንዴ እንደገና ፈጠርከው እኮ … ነፍስ እኮ ነው የዘራህበት! ብራቮ … ብራቮ!” ከንቲባ ሶደሪኒ በደስታ ፈነጠዙ፡፡ እንግዲህ ልብ አድርጉ፡፡ ምንም እንኳ እሱ በኖረበት ዘመን ኖረን በአካል ባናውቀውም፣ ለድፍን አለሙ ሁሉ ትንግርት የሆኑ ስራዎቹን ትቶ ያለፈው ማይክል አንጀሎ በቃ ማይክል አንጀሎ ነው፡፡ ስለዚህ ከንቲባ ሶደሪኒ እንደፈለጉት የቅርፁን አፍንጫ ቢያሳጥረው ኖሮ የዚያ ቅርጽና የእምነበረድ ጥርብ ድንጋይ ነገር አለቀ ደቀቀ ነበር፡፡ ከንቲባ ሶደሪኒን ተሳስተዋል ብሎ በድርቅና ቢከራከራቸውና የልባቸውን መሻት ባይሞላላቸው ኖሮ ደግሞ እሳቸውን ከማስቀየምና ወደፊት ሊሠጡት የሚችሉትን የስራ ኮንትራት ከማስቀረት በቀር የሚያገኘው አንዳችም አይነት ጥቅም አልነበረም፡፡ ማይክል አንጀሎ ግን ነቄ ጥበበኛ ነበረና ዛሬም ድረስ ልክ እንደ አዲስ የጥበብ ስራ መላው አለም የሚያደንቀውን የዳዊትን ቅርጽ ሳይነካ የከንቲባ ሶደሪኒን ፍላጐትም በአጓጉል ክርክር ሳይቃወም ያደረገውን አደረገ - “እንዴ! ቃላቶች በሌላው ሠው ስሜትና ስጋት መጠን፣ የመተርጐም እጅግ አስጠሊታና አደገኛ ችሎታ እንዳላቸው ያወቅሁት ገና
ጥንት እኮ ነው” እያለ፡፡
መቼም ምንም ቢሆን ማይክል አንጀሎን መሆን አንችልም፡፡ ነገር ግን የእሱን ልባምነትና የነገሮችን ቀጣይ ውጤት ምንነት በሚገባ የመረዳት የአዕምሮ ንቁነትን መኮረጅ እንችላለን፡፡ ስራችንን ወይም እምነታችንን ለማስረዳት በምናደርገው የተሟሟቀ ክርክርና ሙግት ጉዳያችንን የሚደግፍ የሚመስለንን ነገር ሁሉ መናገር፣ መጽሀፍ ቅዱስን ወይም ቅዱስ ቁርአን መጥቀስ አሊያም ሊረጋገጥ የማይችል የስታትስቲክስ ቁጥር ሁሉ መጥቀስ እንችላለን፡፡ ቃል ግን ቃል ብቻ ነው፡፡ስራና ተግባር ግን ከሁሉም የበለጠ ትርጉም የሚሠጥና ጠንካራ ነው፡፡ የሠሩትን ወይም የሚሠሩትን በወሬ ወይም በክርክር ሳይሆን በስራ ብቻ ማሳየት እንደ ንግግር ሰው አያስቀይምም፡፡ እንደየሠው ስሜትና ስጋት መጠን እንደተፈለገው አይተረጐምም፡፡ እርግጥ ነው ልጆች ሳለን የክርስትና ሃይማኖት መሪዎች “ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው” እያሉ ቢያስተምሩንም ስመጥሩው ባለቅኔና ፈላስፋ ባልታዛር ግራሽያን “እውነት ባጠቃላይ ይታያል እንጂ የሚሠማው ከስንት አንድ ነው” ያለውም ምንም አቃቂር የሚወጣለት አይደለም፡፡ በመጨረሻ እንዲህ እንላለን፡፡ እንደ ማይክል አንጀሎ የሠራውን ሥራ በዲስኩርና በሙግት ሳይሆን
በተግባር የሚያሳይ አስተዋይ ልበ ብሩህ መሪ ያገኙ ህዝቦች ብፁአን ናቸው፡፡ አሜን!!

 

 

Read 1741 times Last modified on Sunday, 06 May 2012 15:41