Monday, 02 July 2018 13:17

በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(9 votes)

በአለም አቀፍ ደረጃ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በየቀኑ ከወሲብ ጋር ለተያያዘ በሽታ ይጋለጣሉ፡፡
በየአመቱ በአለም አቀፍ ደረጃ ወደ /357/ ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በወሲብ ከሚተላለፉ 4 በሽታዎች ለአንዱ ይጋለጣሉ፡፡ በሽታዎቹም፡- የጨብጥ በሽታ፤ ቂጥኝ፤ የብልት በሽታ እና ክላምዲያ በመባል የሚታወቁት ናቸው፡፡  
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ500 ሚሊዮን ሰዎች በላይ የብልት ቆዳ በሽታ ይኖራቸዋል፡፡
ከ290 ሚሊዮን ሴቶች በላይ ሂዩማን ፓፒሎማ ለተባሉት የቫይረስ ሕመሞች ይጋለጣሉ፡፡
በግብረስጋ የሚተላለፉ በሽታዎች ሲባል ማንኛውም ከመከላከያ ውጭ የግብረስጋ ግንኙነትን የሚፈጽም ሰው ሊያጋጥመው እንደሚችል የሚገመት ነው፡፡ በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል (STI) ወይም (STD) በሽታው ካለበት ሰው ጋር ያለምንም መከላከያ የግብረስጋ ግንኙነት ሲደረግ በሕመ ምነት ከተጠቀሱት መካከል በአንዱ ወይንም በአንድ ጊዜ በተወሰኑ ሕመሞች መያዙ ግድ ነው፡፡ ሕመሞቹም ዋናው ስማቸውና በአገር ቋንቋ የሚታወቁ ሲሆን የሚከተሉት ናቸው፡፡
Chlamydia …..ክላምዲያ ፤
Genital Herpes….የብልት ቆዳ በሽታ፤
Genital Warts…. የብልት ኪንታሮት፤
Gonorrhea …ጨብጥ በሽታ፤
Hepatitis B……. የወፍ በሽታ፤
HIV and AIDS……ኤችአይቪ ወይም አመንምኔ፤
Pubic Lice (or crabs) …. በብልት አካባቢ ቅማል፤
Syphilis…ቂጥኝ፤
Trichomonas…የብልት በሽታ፤ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ከባክቴሪያና ከቫይረስ እንዲሁም ከጥገኛ ትላትሎች ተያያዥ የሆኑ በወሲብ ግንኙነት ምክንያት የሚተላለፉ ሕመሞች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ግን ከላይ የተጠቀሱት በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል በተለይም አራቱ…ማለትም …(syphilis, gonorrhoea, chlamydia and trichomoniasis.) የተሰኙት ይበልጥ የሚከሰቱና ነገር ግን የህክምና እርዳታ ከተደረገላቸው የሚድኑ ናቸው፡፡ የተቀሩት ማለትም ከቫይረስ የሚከሰቱት ማለትም (hepatitis B, herpes simplex virus (HSV or herpes), HIV, and human papillomavirus (HPV) በሕክምናውም ቢሆን ለማዳን አስቸጋሪ የሚባሉ ናቸው፡፡ በእርግጥ ያሉበትን ደረጃ በሕክምናው ማሻሻል ይቻላል፡፡
ከወሲብ ጋር ተያያዥ የሚባሉት በሽታዎች ከሰው ወደሰው የሚተላለፉባቸው መንገዶች በተለ መደው ወይንም ተፈጥሮአዊ በሆነው የወሲብ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በ (ANAL -ORAL) አፍ እን ዲሁም ወንዶች ለወንዶች የወሲብ ግንኙነት በሚፈጽሙበት (ለሴትም ይሰራል) አካል ጭምር በሚኖር ወሲባዊ ግንኙነት ሳቢያ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ጨብጥ ፤ቂጥኝ ፤ክላምዲያ፤ ሄፒታይ ተስ ቢ እና ኤችአይቪ በሽታዎች በእርግዝናና በወሊድ ወቅት ከእናት ወደልጅ ሊተላለፉ ይች ላሉ፡፡   
አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ከተጠቀሱት በሽታዎች አስቀድሞ እራስን መከላከል ወይንም ከተያዙም በሁዋላ ጊዜ ሳያጠፉ ወደ ሕክምናው ከሄዱ መዳን እንደሚቻል ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ዎች በሽታው እንዳጋጠማቸው የሚያሳዩት ነገር ፍርሀትና የብስጭት ወይንም የሐፍረት ስሜት ነው፡፡ ዝም ብሎ መቆየትና መጨነቅ ግን መጥፎ ሀሳብ በመሆኑ ምናልባትም ምልክቱ ታውቆ ለመታከም እድልን የሚነፍግ ወይንም ደግሞ ምናልባት የህመም ምልክቱ ምንነቱን እንኩዋን ባይገልጽ በሽታው ከሰዎቹ ጋር አብሮ እንደሚኖርና መጨረሻው መጥፎ መሆኑ የታ ወቀ ነው፡፡ የህመሙ ምልክትም ከብልት የሚወጣ ፈሳሽ … ከሽንት ቱቦ ጋር የተያያዘ ፈሳሽ ወይ ንም ወንዶችን ከሆነ የማቃጠል ስሜት፤ የሆድ እቃ ሕመም፤ የመራቢያ አካል ሕመም የመሳ ሰሉት ይከሰታሉ፡፡   
በሽታውን አስቀድሞ ለመከላከል ከሚረዱ ነገሮች መካከል ወሲባዊ ግንኙነቱን በጥንቃቄ መፈጸም አንዱ ነው፡፡ በተለይም የወሲብ ግንኙነቱን የሚፈጽሙት ሰዎች እርስ በእርሳቸው ከበሽታው ነጻ መሆናቸውን እርግጠኛ ካልሆኑ በስተቀር እና የወሲብ ግንኙነቱ አንድ ለአንድ መሆኑ በትክክል ካልታወቀ ኮንዶም መጠቀም አማራጭ የሌለው የጥንቃቄ መንገድ ነው፡፡
ኮንዶምን በአግባቡ ለመጠቀም፡-
ኮንዶም በቀዝቃዛና ደረቅ ቦታ የፀሐይ ብርሀን በማይጎዳበት ቦታ ማስቀመጥ፤
ኮንዶም የመበላሸት ቀኑ ከመድረሱ በፊት ብቻ መጠቀም፤
ፓኮውን በጥንቃቄ በመክፈት ጥሩ ብርሀን ባለበት ቦታ ካደረጉት ኮንዶሙ ላይቀደድ ይችላል፡፡ የኮንዶሙን ጫፍ በመያዝ በወንድ ብልት ላይ በትክክል ማስቀመጥ ይገባል፡፡
ኮንዶሙን በድጋሚ አለመጠቀም ያስፈልጋል፡፡አንድ ጊዜ ከተጠቀሙም በሁዋላ በጥንቃቄ ወደቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጣል ተገቢ ነው፡፡
በቀላሉ ሊቀደድ የሚችል አነስተኛ ጥራት ያለው ኮንዶም አለመጠቀም ጥሩ ነው፡፡
ኮንዶምን በመጠቀም ጊዜ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ፈሳሽ ወደሴትዋ ብልት እንዳይገባ ከመጠቀም በፊት የኮንዶሙን ጥራትና ብቃት በሚገባ ማስተዋል እንዲሁም ከጥቅም በሁዋላ መቼ እና እንዴት ማስወገድ እንደሚገባ አስቀድሞ እውቀቱን ማደርጀት ይገባል፡፡ ይህ ከሆነ በወሲብ ግንኙነት ጊዜ ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡
ከመደበኛ ሚስት ወይም ባል ጋር ከኮንዶም ውጭ ያለመከላከያ ወሲባዊ ግንኙነት እንደሚፈጸም እሙን ነው። ነገር ግን ሁለቱም ባልና ሚስት አስቀድሞ እራሳቸውን ማዘጋጀት የሚያስፈልግበት ሁኔታ ይኖራል፡፡
ሁለቱም ባልና ሚስት ሙሉ የጤና ምርመራ በማድረግ ከተላላፊ በሽታ ነጻ መሆናቸው መረጋገጠና አንዳቸውም ከሌላ ሰው ጋር ወሲብ የማይፈጽሙ መሆን አለባቸው፡፡
እርግዝና ለመከላከል ከፈለጉ እንኩዋን ሌላ አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ይህ ካልሆነ በስተቀር ባልና ሚስትም ቢሆኑ እንኩዋን ከበሽታው እራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ በጥንቃቄ የወሲብ ግንኙነት እንዲያደርጉ ይመከራሉ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ በየቀኑ ከ1ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከወሲብ ጋር ለተያያዘ በሽታ የሚጋለጡ ሲሆን ይህ በአመት ሲሰላ ወደ 357/ሚሊዮን አዲስ በኢንፌክሽኑ የተያዙ ሰዎች እንደሚኖሩ ግልጽ ነው፡፡ በተለይም አራቱ ህመሞች…ማለትም ክላምዲያ (131/ሚሊዮን) …ጨብጥ (78/ሚ ሊዮን)…ቂጥኝ (5.6 ሚሊዮን)… የብልት በሽታ(143/ሚሊዮን)ይሆናሉ፡፡ ከወሲብ ጋር የተያያዙ በሽታዎች በተያያዥነት የሚያስከትሉት የጤና ችግር ቸል የማይባል ነው፡፡ ለምሳሌም…
ከእናት ወደልጅ የሚተላለፈው ሕመም በእርግዝና ወቅት ጽንሱን ሊጎዳ ስለሚችል የሞተ ልጅ የመውለድ ወይንም እንደተወለደ የሚሞት ጨቅላ መኖር ወይንም ተፈጥሮአዊ ችግር ያለበት ልጅ እንዲወለድ ማድረግ የመሳሰሉት ሊያጋጥሙ ይችላሉ፡፡
human papillomavirus በተባለው ምክንያት በአለም ላይ በየአመቱ ወደ /528.000/ ያህል ሴቶች በማህጸን በር ካንሰር የሚያዙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ወደ /266.000/ የሚሆኑት በየአመቱ ለሕልፈት ይዳረጋሉ፡፡   
ከወሲብ ጋር በተያያዘ የሚተላለፉ በሽታዎች በሰዎች ላይ እንዳይደርሱ ለማድረግ ተከታታይነት ያለው ትምህርት እና የምክር አገልግሎት ለመላው ሕብረተሰብ መስጠት ያስፈልጋል። በተለ ይም በወሲብ ስራ የሚተዳደሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮንዶምን አጠቃቀም በተገቢው መንገድ እንዲረዱት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በበለጠ ሁሉም ሰው ያለበትን የጤና ደረጃ እንዲያውቅ የሚያስችል ምርመራ ማድረግ እንዲችል አስፈላጊው ምክር በባለሙያዎች እንዲሰጥ ያስፈል ጋል፡፡  
 ምንጭ--WHO/2016-2021

Read 8413 times