Print this page
Sunday, 01 July 2018 00:00

የቤተ መንግሥቱና የጠ/ሚኒስትሩ ጠባቂዎች ተቀይረዋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተፈፀመውን የቦንብ ፍንዳታ ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣ የቤተ መንግስትና የግል ጠባቂዎች ሙሉ ለሙሉ በአዳዲስ አባላት መቀየራቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
በቤተ መንግሥቱ ጠባቂነት ለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩ “የክብር ዘበኞች” ከእነ አዛዦቻቸው ወደተለያዩ የጦር ክፍሎች መበተናቸውን የጠቆሙት ምንጮች፤ በምትኩ አዳዲስና ልዩ ስልጠና የወሰዱ ጠባቂዎች መመደባቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ፤ ጠ/ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ላስመዘገቡት ስኬት ድጋፍና ምስጋና ለማቅረብ ሚሊዮኖች በወጡበት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተከሰተውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ የጥበቃና የደህንነት     ኃይሉ ክፍተት አሳይተዋል በሚል ትችትና ወቀሳ ሲሰነዘር የሰነበተ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ በርካቶች ከኃላፊነት ተነስተው በህግ ጥላ ሥር እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

Read 10155 times