Saturday, 30 June 2018 12:09

“የልብ ቃጠሎ” እና “ንውዘት” ነገ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በገጣሚና ደራሲ አበበ ካብ ይመር የተፃፉት “ንውዘት” የግጥም መፅሐፍና “የልብ ቃጠሎ” የአጫጭር ልቦለዶች ሥብስብ ነገ ከቀኑ 3፡30 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል አዳራሽ ይመረቃሉ፡፡ ንውዘት የግጥም መፅሐፍ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ80 በላይ ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ112 ገፅ ተቀንብቦ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
የልብ ቃጠሎ የተሰኘውም መፅሃፋቸው በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ 12 ያህል አጫጭር ልቦለዶችን የያዘ ሲሆን በ134 ገፅ ተቀንብቦ በ60 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ በዕለቱ ተ/ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋውና ረ/ፕሮፌሰር ደረጀ ገብሬ በመፅሐፍቱ ላይ ዳሰሳ እንደሚያቀርቡና አንጋፋና ወጣት ፀሐፍት ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 4408 times