Print this page
Saturday, 23 June 2018 12:20

EC…በሴት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

 በየአመቱ እንደውጭው አቆጣጠር ሴፕቴምበር 26/አለም አቀፍ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ 214/ሚሊዮን ሴቶች ዘመናዊውን ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ ማግኘት ቢፈልጉም…አልቻሉም፡፡
WHO/2017
Emergency contraceptive …አፋጣኝ የእርግዝና መከላከያ… እውቀት… አመለካከት እና ተግባር በኢትዮጵያ በሴት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዘንድ ምን ይመስላል ?የሚለው ጥናት የተደረገው በተለያየ ጊዜ ሲሆን ጥናቶችን በመፈተሸ ደግሞ አንድ የተጠቃለለ መረጃ የሰፈረው በኢትጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ጆርናል በውጭው አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 2017/ ነው፡፡
ባደጉትም ይሁን በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ከማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያው እና ከጤና ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ባልተፈለገ ጊዜ በሚፈጠር እርግዝና ምክንያት በእናቶችም ይሁን በሚፈጠረው ጽንስ ላይ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል የሚከሰተው ችግር ትኩረትን የሚሻ ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ ባደጉም ይሁን በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት በተለይም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድ የሚከሰተው ያልታቀደ እርግዝና የህብረተሰብ ጤና እንክብካቤን የሚያስተ ጉዋጉል እና ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲያ ቋርጡ እና የወደፊት ሕይወታቸውን በትክክል እንዳይመሩ የሚያደርግ እንቅፋት ነው፡፡  
በተደረጉት የዳሰሳ ጥናቶች እንደተስተዋለው ግማሽ የሚሆኑት ያልታቀዱ እርግዝናዎች የሚከ ሰቱት ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል የሚያስችሉ መንገዶች መኖራቸውን ካለማወቅና ስለአ ጠቃቀማቸውም በትክክ ለኛው መንገድ ትምህርት አለመሰጠቱ እንዲሁም ከተጠቃሚ ዎችም በኩል ይህ ይደርሳል ብሎ ካለማሰብ ወይንም ጥንቃቄ የጎደለው ወሲብ ሲፈጽሙ ሊከሰት ስለ ሚችለው ነገር አስቀድመው አለመገመታቸው ወይንም ስለአሉት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ መንገዶች የተሳሳተ አመለካከት መኖሩ እና ጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጁ ያለመሆን ውጤት ነው፡፡ ምንም እንኩዋን በኢትዮጵያ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ በተለያየ ዘዴ እና ኪስን በማይነካ መልኩ ለሁሉም የቀረበ እና የተለያዩ ፕሮግራሞች ተነድፈው በስራ ላይ ቢሆኑም ብዙ ወጣቶች ግን ያልተፈለገ እርግዝና እንደሚገጥማቸውና ጥንቃቄ የጎደለውም ይሁን በባለሙያ በመታገዝ ጽንስ እንደሚያቋርጡ መረጃዎቹ ያሳያሉ፡፡
Emergency contraceptive (EC) በአማርኛው አፋጣኝ ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ ከሌሎች መከላከያዎች የሚለየው ምንም መከላከያ የማይጠቀሙ ሴቶች ባላሰቡት ጊዜ ወይንም ተገደው የወሲብ ግንኙነት ቢፈጽሙ ጽንሱ ከመፈጠሩ በፊት የሚወሰድ እንክብል በመሆኑ ያልተፈለገ እርግዝናው እንዳይከሰት ስለሚያደርግ ነው ፡፡ ይህም ያልተፈለገ እርግዝናን በመከላከል በዚያ ውም በቤተሰብ ውስጥ የሚወለዱ ሕጻናትን ቁጥር በመቀነስ እና ጥንቃቄ የጎደለው ጽንስ ማቋ ረጥ እንዳይኖር በማድረግ ዋናውን የእናቶች ጤንነት ለመንከባከብ ይረዳል፡፡ ይህ አፋጣኝ ያልተ ፈለገ እርግዝና መከላከያ በትክክል የወሲብ ግንኙነቱ እንደተፈጸመ በ72/ሰአት ጊዜ ውስጥ ከተወሰደ ቢያንስ ቢያንስ 75% የሚሆነውን ያልተፈለገ እርግዝና ለመከላከል ያስችላል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ ሴቶች ስለ (EC) ያላቸው እውቀት… አመለካት…እና ድርጊት ምን ያህል እንደሆነ ሲፈትሹ ካገኙት ውጤት በመነሳት የሚመለከታቸው አካላት ስለጉዳዩ በቂ መረጃ እንዲሰጡ ፤(EC) አቅርቦቱ እንዲጨምር ፤ለአጠቃ ቀሙ ምቹ ሁኔታ እንዲኖር ፤በተፈለገ ጊዜ ሁሉ መገኘት የሚችልበት መንገድ እንዲመቻች እና አጠቃቀሙ ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲፈጸም ማድረግ የሚቻልባቸው መንገዶች እንዲኖሩ ጥቆማ ተደርጎአል፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን ጥናቶች መሰረት ባደረገ መልኩ የተሰራው ይህ መረጃ እንደሚጠቁመው በኢትዮጵያ ውስጥ ለጥናቱ በተመረጡ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ የሴት ተማሪዎች ስለ (EC) ያላቸው ንቃተ ህሊና የተለያየ ነው፡፡ ለጥናቱ ከተመረጡት ውስጥ ከሁለት አምስተኛ በላይ የሚሆኑት መላሾች ስለ አፋጣኝ የወሊድ መከላከያው ምንም አያውቁም ማለት ይቻላል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያለው እውቀት የሚለያይ ሲሆን በከፍተኛ ደረጃ እውቀቱ ያላቸው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (84.2%) ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ (23.4%) ነው፡፡ ይህ ልዩነትም ምናልባት በጥናቱ መረጃ አሰባሰብ ጊዜ መረጃውን የሚያጠናቅሩትና ምላሽ የሚሰጡት ተማሪዎች መራራቅ እንደ አንድ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ከግምት ውስጥ ገብቶአል፡፡  
ወላጆች፤ አስተማሪዎችና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መረጃው ለተማሪ ዎቹ እንዲደርስ ማድረ ጋቸው አስፈላጊ ቢሆንም የሴት ተማሪዎቹ ትክክለኛ አመለካከትም በጉዳዩ ተቀባይነትና አተ ገባበር ዙሪያ ወሳኝነት አለው፡፡ ከዚህም አቅጣጫ ጥናቱ እንደሚያሳየው ምላሽ ከሰጡት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በ(EC) ላይ  የተሳሳተ አመለካት የነበራቸው መሆኑ ተረጋግጦአል፡፡ የዚህም ምክንያት በአፋጣኝ ጊዜ መከላከያው ላይ ንቃተ ህሊናቸው አለመዳበሩ፤ በአፋጣኝ ጊዜ መከ ላከያው አጠቃቀም ዙሪያ  የተሳሳተ እውቀት በመኖሩ ወይንም  ከእምነት ፤ከባህል እና ከማህበራዊ ተቀባይነት አንጻር ሀሳቡን መቀበልና መድሀኒቱን መጠቀም አለመፈለግ ሊሆን ይችላል፡፡
የአፋጣኝ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ እንደመደበኛው የመከላከያ መድሀኒት እንዲወሰድ አይመ ከርም፡፡ አፋጣኝ የእርግዝና መከላከያ በማንኛውም መንገድ እንደመደበኛው ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ የማይመከርበት ምክንያትም ሲሰራም ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታ ወይንም ተገዶ በመደፈር ምክንያት ወሲብ ቢፈጸም ሊፈጠር የሚችለውን እርግዝና እንዳይፈጠር ለማድረግ ሲባል የሆር ሞን መጠኑ ከመደበኛዎቹ መከላከያዎች ከፍያለ እና እንደመደበኛዎቹ መከላከያዎች ጠንካራ ስላልሆነ ነው፡፡ ለምሳሌም አንዲት ሴት የግብረስጋ ግንኙነት ካደረገች ከሁለት ቀን በሁዋላ መከ ላከያውን ብትወስድ ከ20-30% የማርገዝ እድልዋን ላይሸፍን ይችላል፡፡ በጥቅሉም የመድሀኒቱ ያልተፈለገ እርግዝናን የመከላከል አቅሙ ከ70-80% በላይ አይሆንም፡፡ መደበኛዎቹ ግን እስከ 99.5% ድረስ እርግዝናን ይከላከላሉ፡፡ (EC)  በመደበኛነት ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከ ላከል የሚያስችሉት መከላከያዎች በማይወሰዱበት ጊዜ በድንገተኛነት ለሚከሰት ያልተፈለገ እርግዝና መከላከያ እንዲሆን ከጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ሴት ተማሪዎች በ(EC) ላይ ያላቸው እውቀትና አመለካት እንዲሁም ንቃተ ህሊናቸው እና ድርጊት በጣም አነስ ተኛ ወይንም ዝቅተኛ ሲሆን ለዚህም የተመከረው ተማሪዎቹ በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ትኩረት እንዲያ ደርጉና አጠቃቀሙንም እንዲያጎለብቱ ተገቢው መረጃ ሊኖራቸው ይገባል የሚል ነው፡፡ ይህ ከሆነ ያልተፈለገ እርግዝናን መከላከል ፤አላስፈላጊ ወይንም ጥንቃቄ የጎደለው ጽንስን ማቋ ረጥ እንዳይኖር፤እንዲሁም ባልታቀደው እርግዝና ምክንያት በሚኖረው ትምህርትን የማቋረጥ ግፊት የተነሳ የወደፊት ሕይወታቸው እንዳይበላሽ ባጠቃላይም የእናቶችን ጤንነት ከመጠበቅ አንጻር ሰፋ ያለ ስራ መሰራት እንዳለበት ይጠቁማል፡፡
ይህንን የአፋጣኝ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ማንኛዋም ሴት ልትጠቀም ትችላለች ፡፡ ነገር ግን ከጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ በተለይም በሆስፒታሎች ውስጥ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች አሉ፡፡ በተለይም ከጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ከአሁን ቀደም ባገኘኘው መረጃ መሰረት ማንኘኛዋም ሴት ወደሆስፒታሉ አገልግሎቱን ፈልጋ ስትቀርብ፡-
በድንገተኛ ሁኔታ ወይንም በኃይል ጥቃት መደፈሯን መግለጽ፤
እርጉዝ መሆን አለመሆንዋን ማረጋገጥ (ከግንኙነቱ በፊት አስቀድሞውኑ እርግዝና ተከስቶ ከሆነ ምንም ስለማይጠቅም መድሀኒቱ ሊወሰድ አይገባም፡፡ ሴቷ ባልተዘጋ ጀችበት ወይንም በድንገት በፈጸመችው ግብረ ስጋ ግንኙነት ምክንያት ከ72/ሰአት በፊት መድሀኒቱን ለመውሰድ ዝግጁ መሆን አለባት፡፡)
የወር አበባ አይታ ሌላ የወር አበባ ጊዜው ካለፈ (ለምሳሌም የወር አበባዋን ካየች ሁለት ወር ያለፋት መሆኑን ካወቀች ይኼኛውን የአፋጣኝ ጊዜ የእርግዝና መከላከያውን መው ሰድ አያስፈልጋትም፡፡ ምክንያቱም እርግዝና ተከስቶ ሊሆን ስለሚችል ነው፡፡ በተቻለ መጠን የወር አበባዋ ከአራት ሳምንት በላይ የቆየ መሆን የለበትም፡፡)
ማንኛዋም ተጠቃሚ በሆስፒታሉ በ24/ሰአት ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት የምትችል መሆኑን ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡ ምናልባትም ወደሆስፒታል ስለተሄደ ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለማንኛዋም ባለችበት ቦታ ሆና መከላከያውን መጠቀም ለምትሻ ሴት የሚጠቅሙ ናቸው ፡፡
ምንጭ፡-EJRH/2017/Volume 9, number/1/

Read 2494 times