Saturday, 23 June 2018 12:10

“ኢትዮጵያዊ ኮንሰርት 2” ቅዳሜ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በጆርካ ኤቨንት ኦርጋናይዘርስ አዘጋጅነት የሚቀርበውና አንጋፋው ድምፃዊ ክብር ዶ/ር ማህሙድ አህመድና ድምፃዊ አብዱ ኪያር የሚያቀነቅኑበት “ኢትዮጵያዊ ኮንሰርት 2” የዛሬ ሳምንት ቦሌ ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዘመናዊው የቃና ስቱዲዮ አዳራሽ ከቀኑ 12፡00 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡
“በአዲስ ኮንሰርት ሁለት” በጉጉት ተጠብቆ በጤና መጓደል ሳይገኝ የቀረው ማህሙድ አህመድ አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝና ለኮንሰርቱ ዝግጅት አዲስ አበባ መግባቱን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 900 ብር ሲሆን ለጥንዶች 1490 ብር እንደሆነም ታውቋል፡፡ ለኮንሰርቱ 2 ሺህ ሁሉም ቪአይፒ የሆኑ ትኬቶች መዘጋጀታቸውን የገለፁት አዘጋጆቹ ፈጥኖ የገዛ እንደሚስተናገድ ተናገረዋል፡፡ ምግብና መጠጥ ከተማዋ ላይ አሉ የተባሉ ባርና ሬስቶራንቶች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርቡም ተገልጿል፡፡
ጋሽ መሐሙድን አበጋዝ ክብረወርቅ፣ ሄኖክ ተፈራ፣ ግሩም መዝሙር፣ ያሬድ ተፈራና ሌሎችም አንጋፋ የባንዱ አባላት፣ አብዱ ኪያርን ደግሞ መሃሪ ብራዘርስ ባንድ እንደሚያጅቧቸው ታውቋል፡፡

Read 4639 times