በኮሎኔል ፈቃደ ገብረየሱስ የተሰናዳውና በአመራር ሳይንስና ጥበብ ላይ ሰፊ ትንታኔ የሚሰጠው “የአመራር ሳይንስና ጥበብ” መፅፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡
“የሁሉን ነገር መውደቅም ሆነ መነሳት የሚወስነው አመራር ነው” የሚለው የጆን ማክስዌልን አመራር ተንተርሶና የተለያዩ ውጤታማ ተሞክሮ ያላቸውን አመራሮች ልምድ ቀምሮ የተዘጋጀው መፅሀፉ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አመራር ያለውን ጉልህ ሚና በማስተማር ሰዎች ቢዝነሳቸውን፣ ቤተሰባቸውን እና ተቋማትን እንዴት መምራት እንደሚችሉ ጥበብን ያላብሳል ተብሏል በ704 ገፅ የተቀነበበው መፅሀፉ በ300 ብር ለገበያ ቀርቧል ደራሲው ከዚህ ቀደም “ስትራቴጂ” የተሰኘው የቢዝነስ ስትራቴጂን እውቀት የሚያስጨብጥ መፅሀፍ ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል፡፡
Saturday, 23 June 2018 12:08
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና