Saturday, 23 June 2018 12:04

“ደቦ” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


   ከተለያየ የሙያ ዘርፍ የተውጣጡ 60 ነባርና አዳዲስ ፀሐፍት የተሳተፉበት “ደቦ 60 ደራሲያን” የተሰኘ መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡
በዚህ መፅሀፍ ላይ ደራሲያን፣ ገጣሚያን መምህራን የሙዚቃ ባለሙያዎች፣ ተዋንያን፣ ጋዜጠኞች እና በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦች ያበረከቷቸው ወጎች፣ አርቲክሎች ግጥሞች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎችና መሰል ፅሁፎች ተካትተውበታል፡፡ በዛጎል መፃህፍት ተዘጋጅቶ በደራሲ እንዳለ ጌታ ከበደ አርትኦቱ የተሰራለት መፅሀፉ በ516 ገፅ ተቀንብቦ በ170 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 5895 times