Saturday, 23 June 2018 11:44

የሠማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተመካከሩ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(7 votes)

 በታሰሩ ግለሰቦች፤ በተፈናቀሉ ዜጎች፣ በፍትህ… ዙሪያ ውይይት ተደርጓል

   የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አስፋን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ትናንት አርብ በባህር ዳር ተገኝተው፣ ከአማራ ክልላዊ መንግስት ርዕሠ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በክልሉ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸው ተገለፀ፡፡
በዚህ የምስክር መድረክ ላይ በዋናነት በእስር ምክንያት ከስራ ገበታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መደበኛ የመንግስት ስራ በሚመለሡበት ሁኔታ፣ እስር ቤቶችን በመፈተሽ በእስር የተረሡ ወገኖች መልቀቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበበ አካሉ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና  24 አመት ሙሉ በእስር ላይ የሚገኙ የሃይማኖት ሊቅ በሚለቀቁበት ሁኔታ ላይም መወያየታቸውን የጠቆሙት ሃላፊው፤ የሠማያዊ ፓርቲ አባል የነበረውና ባልታወቁ ሠዎች የተገደለው ሣሙኤል አወቀ ጉዳይ ፍትህ እንዲያገኝም መግባባት ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ከሌላ ክልል የተፈናቀሉ የክልሉ ተወላጆች በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረናል ያሉት አቶ አበበ፤ ፓርቲው በአካባቢው በሚንቀሣቀሥበት ወቅት ወከባ እንዳይፈፀምበት ውጤታማ ምክክር መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

Read 8670 times