በገጠሚና ደራሲ ትዘዘው ክንዴ የተፃፉ የግጥም ስብስቦችን ያካተተው “አለንጋ” የተሰኘ የግጥም መድብል ነገ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቤተ-መፃህፍትና ቤተ- መዛግብት ኤጀንሲ አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በዕለቱ ገጣሚያን ስራቸውን እንደሚያቀርቡና ከመፅሐፉ የተመረጡ ግጥሞች እንደሚነበቡ የታወቀ ሲሆን በምርቃቱ ላይ በርካታ ደራሲያን፣ ገጣሚያን፣ የግጥም አድናቂዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡