Sunday, 17 June 2018 00:00

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(5 votes)

የሃረሪ ክልላዊ መንግስትን ላለፉት 15 አመታት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ሙራድ አብዱላዲ፤ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ፡፡
አቶ ሙራድ አብዱላዲ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ የሃረሪ ክልልን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከስልጣን የሚለቁበት ምክንያት ግን አልታወቀም፡፡
ምንጮች በበኩላቸው ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ከክልሉ የህዝብ ተወካዮች ጋር ባካሄዱት ውይይት ላይ በክልሉ የመልካም አስተዳደር ችግር መስፋቱ፣ ብሄርተኝነትና ጎሰኝነት መንሰራፋቱ ይህም የግጭት መንስኤ እየሆነ መምጣቱ በህዝቡ ተነስቶ እሳቸው ላለፉት 15 ዓመታት ከቆዩበት ስልጣን እንዲነሱ መጠየቃቸውን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሃረር ከተማና አካባቢዋ የተለያዩ ግጭቶችና ተቃውሞዎች ሲከሠቱ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ሣምንት ከመሬት ይገባኛል ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ግጭት፣ በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ሲሆን የሆቴል ኢንቨስትመንቶችም ለቃጠሎ መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡
የክልሉ መንግስት ምክር ቤት፣ አቶ ሙራድን የሚተካውን ቀጣዩን የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 4159 times