Sunday, 10 June 2018 00:00

“አንዲር 7” የሙዚቃ ትርኢት ማክሰኞ ይቀርባል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)


    መሶብ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ ከብሔዊ ቴአትር ጋር በመተባበር፣ 7ኛውን ዙር “አንዲር የሙዚቃ ትርኢት” የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር እንደሚያቀርብ የባንዱ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አርቲስት ጣሰው ወንድም አስታወቀ፡፡
በዕለቱ በባንዱ የተቀነባበሩ  አዳዲስ ሙዚቃዎች፣ በ8 ሴት ድምፃዊያን የሚቀርቡ ዜማዎች እንዲሁም የዳንስ ትርኢት እንደሚቀርብ የተገለፀ ሲሆን በሙዚቃ ትርኢቱ ላይ ለመታደም መግቢያው ነፃ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 2518 times