Sunday, 10 June 2018 00:00

ጠ/ሚ ዐቢይ ዛሬ በኡጋንዳ የክብር ሜዳሊያ ይሸለማሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

በዛሬው እለት “የጀግኖች ቀን” በታላቅ ድምቀት የምታከብረው ኡጋንዳ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሃገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት  ታበረክታለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት ጀምሮ በኡጋንዳ ይፋዊ ጉብኝት እያደረጉ ሲሆን ዛሬ በሀገሪቱ በብሪምቦ ክፍለ ግዛት በሚከበረው የጀግኖች ቀን በአል ላይ ለአፍሪካ ነፃነት የታገሉ አፍሪካውያን መሪዎች የሚሸለሙትን ከፍተኛ ሜዳሊያ ይሸለማሉ ተብሏል፡፡
የኡጋንዳ የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ኢስቴር ማባዮ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለፁት፤ “The Most Excellent Order of the Pearl of Africa The Grand Master” የተሰኘው ልዩ የክብር ሜዳሊያ ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚበረከተው ለሃገር ሰላምና ለዜጎች ለሰጡት ክብር እውቅና እንዲሆን ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የክብር ሜዳሊያው ለኢኳቶሪያል ጊኒው ፕሬዚዳንት ቴዎዶሮ ባሳንጎ መሰጠቱን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ዶ/ር አብይ ሁለተኛው ተሸላሚ የሃገር መሪ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

Read 3899 times