Print this page
Sunday, 10 June 2018 00:00

የአልጀርሡ ስምምነት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ለህዝብ ውሣኔ መቅረብ አለበት ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(7 votes)

የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ግጭትን የዳኘው የአልጀርሡ ስምምነት ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ለህዝብ በውሣኔ መቅረብ ነበረበት ያሉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ በተግባራዊነቱ ላይ ገዥው ፓርቲ ብቻውን መወሠን አይችልም ብለዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ መግለጫ የሠጠው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፤ የአልጀርሡ ስምምነት ተግባራዊ መደረጉ ከሁለቱ ህዝቦች ግንኙነትና ከኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ጥቅም አንፃር ተገቢ መሆኑን ገልፆ፤ “ነገር ግን ኢህአዴግ ብቻውን ይህን የሉአላዊነት ጉዳይ የመወሠን ስልጣን ማን ሠጠው?” ሲል ጠይቋል፡፡
ፓርቲው በጉዳዩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ወይም የሚኒስትሮች ም/ቤት ተወያይቶ ሊወስንበት ይገባ ነበር ብሏል፡፡
የኢህአዴግ ውሳኔ የህዝብ የስልጣን ባለቤትነትና የአካሄድ ጥያቄ ያስነሣል ያለው ኢራፓ እንዲህ አይነቱ የሃገር ሉአላዊነትና ጥቅም ጉዳይ ለህዝብ ውሣኔ መቅረብ እንዳለበት አስገንዝቧል፡፡
መኢአድ እና ኦፌኮም ተመሳሳይ አቋም ያራመዱ ሲሆን አረና በበኩሉ ተቃውሞውን በተለያዩ ከተሞች በሚያደርገው ሠልፍ እንደሚገልፅ አስታውቋል፡፡
በትናንትናው  እለትም የኢሮብ ማህበረሠብ በሠልፍ ተቃውሞ አሠምቷል፡፡

Read 4323 times