Saturday, 02 June 2018 12:01

“ዐምደ ግእዝ” መፅሐፍ ለገበያ ቀረበ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በደራሲ መምህር ዐቢይ ለቤዛ የተዘጋጀውና በግእዝ ቋንቋ የተሻለ ዕውቀትና ክህሎት ያስጨብጣል የተባለው “ዐምደ ግእዝ” የተሰኘ መፅሃፍ ለገበያ ቀረበ፡፡
“የማንነታችን ሚስጢር፣ የእድገትና ሥልጣኔ ቁልፍ፣ የምግባሮቻችን ምንጭ፣ የአገር ህልውና፣ የነፃነት መንበር፣ የመንፈሳዊና ዓለማዊ ዕውቀት ማህደር የሆኑ ጥልቅና ድንቅ የዕውቀትና ጥበባት ድርሳኖቻችንን፣ መቆፈር፣ ማበጠር፣ መመርመር” እንዳለብን የሚመክሩት ደራሲው፤ ለዚህም ዋናውና ቀዳሚው መሣሪያ የግእዝ ቋንቋን ማወቅ በመሆኑ፣ ሁሉም ሰው ባለበት ራሱን እንዲያስተምር፣ መፅሃፉ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ “ዐምደ ግዕዝ” በ200 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በሁሉም የመጻሕፍት መደብር እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

Read 2227 times