Sunday, 03 June 2018 00:00

አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ሊፈቀድ ነው

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡበት እድል ሊመቻች እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ሰሞን በኢትዮጵያ የ2 ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ካደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በነበራቸው ውይይት፣ ሩዋንዳ ሁሉም አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ሃገሯ እንዲገቡ ያስተላለፈችውን ውሣኔ አድንቀው፣ ኢትዮጵያም በቅርቡ የሩዋንዳን በጎ ተሞክሮ ትከተላለች ብለዋል፡፡
የአፍሪካ መዲና ወደ ሆነችው አዲስ አበባ፣ አፍሪካውያን ያለ ቪዛ እንዲገቡ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሃገሪቱን የቱሪስት ፍሠት የሚጨምር ከመሆኑም በላይ ለኢኮኖሚዋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሉም አፍሪካውያን ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቪዛ እንዳይጠየቁ ሊደረግ እንደሚችል ከመጠቆማቸው ውጭ እንዴትና መቼ ተግባራዊ ይደረጋል በሚለው ላይ ያሉት ነገር የለም፡፡


Read 2537 times